ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 26/2012

0
715

1-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የ2019 የኖቤል የሰለም ሽልማትን በመጪው ማክሰኞ ኅዳር 30/2012 ኖርዌይ ኦስሎ በመገኘት ይቀበላሉ።በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የኖቤል ኮሚቴው የሰላም ሽልማቱ ይበረከታል ተብሎ ይጠበቃል።ጠቅላይ ሚኒስትር በኖርዌይ ቆይታቸው ከአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልቤርግ እና ከንጉስ ሃራልድ 5ኛ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ሲሆን የአገሪቱን የሕዝብ እንደራሴን ይጎበኛሉ ተብሏል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)
………………………………………………………………..
2-የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አገልግሎት እየሰጠ ያለ አንድ የኤም አር አይ የሕክምና መሣሪያ ቢኖረውም ለማሽኑ ክትትልና ጥገና የሚያደርግ፣ ልዩ ስልጠና የወሰደ ባለሙያ እንደሌለው የሆስፒታሉ የባዮ ሜዲካል ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ኢንጂነር ለማ ቁንቢ አስታወቁ።በየቀኑ ከመላው አገሪቱ ለሚመጡ ከ30 በላይ ታካሚዎች የኤም አር አይ የምርመራ አገልግሎት የሚሰጥ ቢሆንም መሣሪያው ለብልሽት ሲዳረግ ፈጣን ጥገና በማድረግ አገልግሎት እንዲሰጥና አገልግሎት ፈላጊውም ሳይጉላላ አገልግሎቱን እንዲያገኝ የሚያደርግ የሰለጠነ ባለሙያ እንደሌለው ተናግረዋል።(ዋልታ)
………………………………………………………………..
3-በፌዴራል ደረጃ የኢህአዴግና የአጋር ፖለቲካ ድርጅቶች አመራር አባላት በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና መሰረታዊ እሳቤ ላይ እየተወያዩ ነው።እየተካሄደ ባለው መድረክ የኢህአዴግ መልካም ድሎች፣ አደረጃጀትና የውህደት አስፈላጊነት የሚያሳይ የውይይት መነሻ ሃሳብ ቀርቧል።(ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
………………………………………………………………..
4-በቅርቡ በኢትዮጵያ በ5ቱ ክልሎችና በድሬዳዋ አካባቢዎች ተከስቶ በርካታ ጉዳት አድርሶ የነበረውን የአንበጣ መንጋ መከላከል መቻሉን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።የአንበጣ ወረርሽኙ በአገሪቱ በተለይም በአማራ፣ ትግራይ፣ ሶማሌ፣ አፋር እና በኦሮሚያ ምስራቅና በምእራብ ሐረርጌ አካባቢዎች በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን በአሁን ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋሉን የግብርና ሚኒስቴር የእፅዋት ጥበቃ ዳይሬክተር ዘብዴዎስ ሰላቶ ገልጸዋል፡፡(ኢቢሲ)
………………………………………………………………..
5-የመከላከያ ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ቲቦር ናጅ ጋር በአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማልያ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለቀጣናው ገንቢ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሆነም ተገልጿል።(ኢዜአ)
………………………………………………………………..
6-በጋላፊ የጉሙሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ላይ ያለው የፍተሻ አገልግሎት ለእንግልት እንደዳረጋቸው የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ተናገሩ።አሽከርካሪዎቹ ደረቅና ፍሳሽ ጭነቶችን ከጅቡቲ ወደ ሀገር ወስጥ የሚያስገቡ ሲሆኑ በጋላፊ የጉሙሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ የፍተሻ አገልግሎት ለማግኘት እስከ ሁለት ቀናት መቆየት እንደሚጠይቅ ገልጸዋል። (ፋና ብሮድካስቲንግ)
………………………………………………………………..
7- በኢትዬጵያ ከትራፊክ አደጋ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 12 ሰዎች ህይወታቸው እንደሚያልፍ ተገለፀ። (ኢዜአ)
………………………………………………………………..
8-የጁባ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ሰራተኞች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ አሻራቸውን ለማኖር በትናንትናው ዕለት በድምሩ የ5 ሺሕ 7 መቶ የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ገዝተዋል።(ኢቢሲ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here