በኢትዮጵያዊው የሚመራው ቦይንግ አፍሪካ ዋና መስሪያ ቤቱን አዲስ አበባ ላይ ይከፍታል 

0
265

ሐሙስ ግንቦት 15 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የአሜሪካው ግዙፍ የኤሮስፔስ ኩባንያ ቦይንግ የአፍሪካ መቀመጫውን እስከ ቀጣዩ ዓመት ድረስ ወደ አዲስ አበባ ያዘዋውራል።

ከስድስት ወራት ገደማ በፊት ኢትዮጵያዊውን አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ዋና ስራ አስኪያጅ አድርጎ የሾመው ቦይንግ አፍሪካ አሁን እየሰራ ከሚገኝበት ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ወደ አዲስ አበባ እንደሚዘዋወር ይፋ ተደርጓል።

ይህ ይፋ የተደረገው በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ በሚገኘውና ዛሬ በሚጠናቀቀው የአፍሪካ አቪዬሽን ጉባዔ ላይ መሆኑን አዲስ ማለዳ ሰምታለች።

ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት አምባሳደርነት ያገለገገሉት እንዲሁም በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የስራ ዘመን ያላቸው አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ተቋሙን እንዲመሩ መሾማቸው ዋና መስሪያ ቤቱ እንደሚዘዋወር ፍንጭ ነበር የሚሉ ዘገባዎች ወጥተዋል።

የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚህ ዓመት ከቦይንግ ኩባንያ ተጨማሪ 20 አውሮፕላኖችን ለመግዛት መስማማቱ አይዘነጋም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በፈረንጆች 2019 ለ157 ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነው ቦይንግ ኩባንያ ለሟች ቤተሰቦች ካሳ እየከፈለ ይገኛል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here