ኢትዮጵያዊው አድማሱ ታደሰ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የባንክ ባለሞያ ክብርን አገኘ 

0
208

ረቡዕ ግንቦት 21 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በትላንትናው ዕለት በኬንያ ናይሮቢ የተደረገው ዓመታዊው የአፍሪካ የባንኮች ሽልማት ስነ ስርዓት ከአፍሪካ የልማት ባንክ ዓመታዊ ጉባዔ ጎን ለጎን ተካሄዷል።

የንግድና ልማት ባንክ ቡድን ፕሬዝዳንትና ዋና ስራ አስፈጻሚ አድማሱ ታደሰ የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ የባንክ ባለሞያ ሽልማትን ተረከቡ። ኢትዮጵያዊው አድማሱ ታደሰ የሚመሩት የንግድና ልማት ባንክ በርካታ ፕሮጀክቶችን በምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የሚያስተዳድር ሲሆን በሞሪሽየስ፣ ቡሩንዲ፣ ኢትዮጵያ እና ዚምባብዌ ቢሮዎች አሉት።

አፍሪኤግዚም ባንክ የዓመቱ ምርጥ ባንክ ሆኖ ሲመረጥ የዓመቱ ምርጥ የብሔራዊ ባንክ ገዢ የኬንያው ካማው ቱጊ ሆነዋል። የዓመቱ ዘላቂ ክንውን ያለው ባንክ ስታንዳርድ ባንክ ግሩፕ አሸናፊ ሲሆኑ በሌሎች ዘርፎችም አሸናፊዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

የአፍሪካ ባንኮች ሽልማት (African Banker Awards) በአህጉሩ ውስጥ ለባንክ ዘርፉ እድገት አስተዋጽዖ ያደረጉ ተቋማት እና ግለሰቦች እውቅና የሚገኙበት መድረክ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here