“አገር የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ኹኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ አይቻልም” ሲል እናት ፓርቲ አስታወቀ 

0
313

👉🏿 በዚህ ሁኔታ “በምክክሩ ለመሳተፍ እቸገራለሁ”

ዓርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአገር አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን የምክክር መድረክ አስመልክቶ “አገር በከፍተኛ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ባለችበት ኹኔታ ምክክርም ጦርነትም በአንዴ ማድረግ የሚቻል አይደለም” ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ።

ፓርቲ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ “ከአገራት ተሞክሮ እንዲህ ባለ ኹኔታ የሚደረግ ምክክርም ውጤታማ እንደማይሆን ታውቆ በተቃራኒ ወገን የተሰለፉ ወንድማማቾችን እያጨራረሰ የሚገኘው የእርስ በርስ ጦርነት በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሄ ሳይበጅለት ምክክሩ አገራችን በእጅጉ የምትሻውን አገራዊ መግባባትና ዘላቂ ሰላም ያስገኝላታል ብለን አናምንም” ማለቱን አዲስ ማለዳ ተመልክታለች።

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት በየእሥር ቤቱ ታስረው ፍትሕ ተነፍጓቸው የሰቆቃ ሕይወት በሚገፉበት፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የማኅበረሰብ አንቂዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎችና ለምክክሩ ጭምር ጉልህ አስተዋጽዖ ማድረግ የሚችሉ ዜጎች ያለ ፍርድ በየእሥር ቤቱ ባሉበት እንዲሁም አገር በአስችኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ባለችበት መደረጉ አግባብ አለመሆኑን እናት ፓርቲ አጽዖት ሰጥቷል።

እንዲሁም በምክክሩ ከመሳተፍ ራሳቸውን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከሂደቱ ያገለሉትን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ምክክር ማምጣት ባልተቻለበትና ሌሎች ምክንያቶች ባሉበት አጠቃላይ በአገር አቀፍ ደረጃ ምክክር እስከሚደረግበት ባለው ጊዜ በቀዳሚነት መፍትሄ አግኝተው ሊፈቱ ካልቻሉና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ካልተቻለ ፓርቲው በምክክሩ ለመሳተፍ የሚቸገር መሆኑን አስታውቋል።

ፓርቲው ከዚህ ቀደም የአገራችን ክፍሎች የተፈጠረው የእርስ በርስ ጦርነት ባልተፈታበት ትርጉም ያለው ምክክር ማድረግ እንደማይቻል መግለጹን አስታውሷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here