የአማራ ክልል ቀውስ እንዲፈታ በጦር አመራሮች የሚመራ ድርድር ዋጋ ሊሰጠው ይገባል- ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ

0
462

👉🏿 መከላከያ ለግጭቱ ቅርበት ስላለሁ የአገር ውስጥ ግጭት እንዲቆም ፍላጎት አለው

ረቡዕ ሰኔ 19 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) አንጋፍው ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ በጦር አመራሮች የሚመራ የሰላም ሂደት ጥሩ አማራጭ እንደሆነ ገለጹ።

ፖለቲከኛው በዛሬው ዕለት በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው እንደጻፉት “በአማራ ክልል የተፈጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አመራር ጥሪውን አጠናክሮ ለመቀጠል ያሳለፈው ውሳኔ በቁም ነገር መታየት አለበት”።

ጃዋር መሀመድ በዝርዝር የትኛዎቹ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች መልዕክትን በተመለከተ እንደጻፉ ባይጠቀስም፤ ፖለቲከኛ መከላከያ ሠራዊት “ለትጥቅ ግጭቶች ፖለቲካዊ መፍትሄዎችን ለማግኘት እውነተኛ ቁርጠኝነትን ያሳየ አንድ የመንግስት አካል ነው” በማለት ገልጸውታል።

የሠራዊቱ አመራሮች በትግራይ ጦርነት ወቅት “ከትግራይ ጦር አዛዦች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ለመገናኘት ወደ ሲሸልስ የበረሩ” መሆናቸው በፖለቲከኛው ጽሁፍ እንደማሳያ ተወስዷል።

ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር የተደረጉትን ሁለት ዙር ንግግሮች እንዲደረጉ ሁኔታውን የፈጠረውም በዋናነት የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች እንደሆኑ ጃዋር መሀመድ ጽፈዋል።

እንደ ጃዋር መሀመድ ገለጻ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በክልሉ ያለውን ግጭት ለመቋቋም ኃላፊነት እንደተሰጠው አካል ስለ ሁኔታው ​​ተጨባጭ ግምገማ ያለው በመሆኑ “የአገር ውስጥ የትጥቅ ግጭቶችን ማቆም ይፈልጋል”።

በተጨማሪም፣ ገዥው ቡድን በጦር ኃይሉ ላይ የበለጠ ጥገኛ እየሆነ በመምጣቱ፣ የአመራሮቹ አስተያየት “አሁን ከበፊቱ የበለጠ ክብደት አለው” ያሉት ፖለቲከኛው፤ የፋኖ አዛዦች እና የአማራ የማህበረሰብ አንቂዎች (አክቲቪስቶች) ይህንን በክልሉ ያለውን አስከፊ ግጭት ለማስቆም በጦር ኃይሎች የሚመራውን የሰላም እርምጃ እንዲቀበሉት በአጽንዖት ጠይቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here