የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው ምን አሉ? 

0
281

ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ከአገራዊ ምክክር በፊት “እምነት መገንባት” ይቀድማል፤መንግስት በህዝብ ዘንድ አመኔታ አልፈጠረም ብለን እናስባለን፤ ለዚህም ማሳያው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ነው ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የፓርላማ አባሉ ተናግረዋል። በጅምላ የንጹሀን ግድያን ጨምሮ ዘረፋ፣ ውድመት፣ እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በአማራ ክልል ተንሰራፍቷል ብለዋል።

በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳቢያ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም ዜጎች በማንነት እየተለዩ እየታሰሩ ነው በማለትም የባልደረባቸውን ክርስቲያን ታደለ ጉዳይ በማንሳት የመንግስትን ሀብት ከምዝበራ የመጠበቅ ሀላፊነትን ወስዶ ሲሰራ የቆየን ሰው ለአንድ ዓመት ገደማ በእስር እየማቀቀ ነው ብለዋል። ከብልጽግና መንግስት ጋር አብረው እየሠሩ የሚገኙ ሰዎችም ስህተት አለ በማለታቸው ታስረዋል፤ ሀብታሙ በላይነህ የተባለው የአብን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልም ለአራት ወራት የት እንዳለ የማይታወቅ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እንዲሰጡ እንማጸናለን ብለዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here