የግል አውቶሞቢሎች የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት የሚችሉበት ሁኔታ እየተጠና መሆኑ ተገለጸ

0
358

ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት እየሰጡ ባሉት ማብራሪያ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየውን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት የግል አውቶሞቢሎችን ወይም በተለምዶ 2 ቁጥር የሰሌዳ መለያ ያላቸው ተሽከርካሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርግ አሰራር እንደሚዘረጋ አስታውቀዋል፡፡

መንግስት ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ ነዳጅ ለማስገባት ወጪ እንደሚያደርግ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህም ሆኖ የትራንስፖርት ችግሩን በተፈለገው ልክ ሊያቃልለው አልቻለም ብለዋል፡፡

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ገለጻ መንግስት ሁሉንም ተሸከርካሪዎች በድጎማ ስርአት ውስጥ እንዲያልፉ የማድረግ አቅም የለውም ያሉ ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡት ተሸከርካሪዎች በላይ የግል አውቶሞቢሎች ከፍተኛውን የነዳጅ ድርሻ መውሰዳቸውም ችግሩን አባብሶታል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታትም የግል አውቶሞቢል ባለንብረቶች የትራንስፖርት ዘርፉን እንዲያግዙ የሚያደርግ አሰራር ይዘረጋል ብለዋል፡፡

በአማኑኤል ጀንበሩ

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here