በአማራ ክልል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች የደንበኞችን የቴሌኮም ፍላጎት ማሟላት በተፈለገው መንገድ እየተከናወነ አለመሆኑ ተገለጸ፡፡

0
190

የኢትዮ-ቴለተኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ2016 ዓመታዊ የተቋሙን የስራ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ላይ እንደ አማራ ክልል ባሉ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የደንበኞች የቴሌኮም ተደራሽነትና የፍላጎት ሁኔታን የማጣጣም ስራ በተገቢው መንገድ አለመሰራቱን አንስተዋል፡፡

በክልል የተፈጠረው ችግር ተቋሙ ተገቢውን ጥቅም እንዳያገኝ እንዲሁም የደንበኞች ፍላጎት በተገቢው መንገድ እንዳይስተናገድ አድርጎታል ብለዋል፡፡

ለመሆኑ በክልሉ በተፈጠረው የሰላም እጦት የደረሰው የቴሌኮም ውድመት በአሃዝ ሲሰላ ምን ያህል ነው የሚለውን ጥያቄ ከመግለጽ የተቆጠቡት ስራ አስፈጻሚዋ የቴሌኮም አውታሮችንና አገልግሎቶችን ወደነበሩበት ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቋማቸው እየተነጋገረ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮ-ቴሌኮም በ2016 የበጀት አፈታጸም ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱ የተገለጸሲሆነብ ይህም የእቅዱን 108.7 በመቶ እንዲያሳካ እንዳደረገው ወ/ሪት ፍሬህይወት በማብራሪያቸው ጠቁመዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here