የአሜሪካ ዶላር በ74.7 ብር እየተገዛ በ76.2 እየተሸጠ ነው
ሐምሌ 22 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በዲሱን የምንዛሬ ተመን ዛሬ ተግባራዊ ማድረግ ጀምረዋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ማሻሻውን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫው የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወስንበት የገበያ ሥርዓት መሸጋገሩን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ባወጣው የውጭ ምንዛሬ ተመን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ74.7364 ብር እየተገዛ በ76.2311 እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊነትን ተከትሎ በምንዛሬ ተመን በአንድ ዶላር ላይ በአማካይ የ18 ብር ጭማሪ ታይቷል።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የምንዛሬ ዋጋ አንድ ፓውንድ ሰተርሊንግ 91.8787 ብር እየተገዛ በ93.7263 ብር እየተሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
እንዲሁም አንድ ዩሮ 81.0367 ብር እየተገዛ በ82.6574 ብር እየተሸጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ያወጣው የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰንጠረዥ ያሳያል።



