ሐምሌ 22 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) 87 በመቶ የሚሆኑት የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዘንድሮውን የመውጫ ፈተና ማለፍ አለመቻላቸውን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገለጹ፡፡
በዚህም 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ማሳለፍ የቻሉት 13 በመቶ ብቻ ነው ማለታቸውን የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን መረጃ አመላክቷል፡፡
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ ማሳለፋቸውን ገልጸዋል፡፡



