የህወሃት የጉባኤ ዝግጅት አወዛጋቢነት ዛሬም ቀጥሏል

ማክሰኞ ነሐሴ 7 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሚገኙባቸው በርካታ የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት በተቃውሞ እና በሌሎችም ምክንያቶች የማይሳተፉበት የድርጅቱ ማእከላዊ የቁጥጥር ኮሚሽን እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ እውቅና የነፈጉት 14ኛው የህወሓት ጉባኤ ዛሬ ማክሰኞ ነሀሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት በይፋዊ የመክፈቻ ስነ-ሰርዓት በመቐለ መካሄድ እንዲጀምር ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተቆርጦለታል።

ጉባኤውን አስመልክቶ የተሰራጨው መርሃ ግብር እንደሚጠቁመው ከዛሬ ነሀሴ 7 እስከ 12 / 2016 ዓ.ም ባሉት 6 ቀናት ይከናወናል።

የህወሓት ፅህፈት ቤት እና ማህተም የተቆጣጠረውና በሊቀመንበሩ (ዶ/ር) ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ሃይል ጉባኤውን በመቐለ በሰማእታት አዳራሽ ” የመዳን ጉባኤ! ” በሚል መሪ ቃል ነው የሚያካሂደው።

በጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንትና በድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ የሚመሩት 14 የማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ደግሞ ” ጉባኤው ህወሓት የሚያጠፋ ፣ ለትግራይ ህዝብ ሌላ ችግርና የእርስ በርስ ግጭት የሚጋብዝ አደገኛ ጉባኤ ” በማለት በይፋ ባወጡት መግለጫ መቃወማቸው የሚታወቅ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here