ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ይቅርታ ጠየቀች

0
523

ቅዳሜ ነሐሴ 18 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)   የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለተናገረችው ንግግር የኢትዮጵያን ህዝብ እና ገዛኸኝ አበራን ይቅርታ ጠይቃለች፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ በድብቅ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ ለተሰራጨው ንግግር የኢትዮጵያን ህዝብ እና ገዛኸኝ አበራን ትልቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ!” ስትል ተማጽናለች፡፡

“ለቀልድና ጨዋታ የተናገርኩት ነው ፣ ከባርሴሎና ጀምሮ ህይወቴን የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀዋል” ያለችው አትሌቷ በክፋት የተናገርኩት አይደለም ለዚህም ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ ማለቷን አዲስ ማለዳ አሰምታለች፡፡

ረዳት ኮምሽነር ደራቱ በማከልም “የገዛኸኝ አበራ ቤት ድረስ ሄጄ ይቅርታ እጠይቃለው ፣ ያም ብርታት አለኝ” ስትል ይቅርታ ለመጠየቅ ያላትን ቁርጠኝነት ጠቁማለች።

በድብቅ ተቀድቶ በማህበራዊ ሚዲያ በስፋት በተሰራጨው ድምጽ አትሌት ገዛኸኝ አበራ “በስናይፐር ይጠበጠባል” የሚል ቃል መናገሯ ይታወሳል፡፡

አትሌት ገዛኸኝ አበራ አትሌት ደራርቱ በማህበራዊ ሚዲያ ገዛኸኝ አበራ “በስናይፐር ይጠበጠባል” ማለቷን ተከትሎ አትሌቱ ህይወቴ አደጋ ላይ ነው በሚል ስጋቱን መግለጹ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here