የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን እና ውዳሴ የምርመራ ማዕከል አዲስ የስፖርት ህክምና ማዕከልን ለመክፈት ተስማሙ

0
275

አርብ ነሐሴ 24 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ላለፉት ሶስት አመታት በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ስር ያሉ ተጫዋቾችን በመመርመር ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ጋር በጋራ ሲሰራ የቆየው ውዳሴ ህክምና ማዕከል አሁን ደግሞ ከፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር የስፖርት ክሊኒክ ለመክፈት ተስማምቷል::

ዛሬ በተካሄደው የፊርማ ስነ ስርአት ላይ ሀሳባቸውን የገለፁት የውዳሴ ምርመራ ማዕከል መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳዊት ሃይሉ ” የስፖርት ክሊኒክን በመክፈት በጣም የምንወዳቸው እንቁ ተጫዋቾቻችን ጉዳት ሲያጋጥማቸው ብቻ ሳይሆን ይህ ከመድረሱ በፊት ምርመራ በማድረግ እና ጉዳት ቢያጋጥምም እንኳን በቂ ህክምና የሚሰጥበትን አሰራር ለመስራት እንዳቀዱ ተናግረዋል:: ”

” በሜዲካል ዲፓርትመንታችን አማካይነት በተደረገው ስምምነት ብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች ሲጎዱ ብቻ ሳይሆን ከዛም በፊት ምርመራ ሲደረግ ነበር” በማለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከዚህ በፊት የነበረውን ስምምነት አስታውሰዋል:: አክለውም ምርመራዎቹ በገንዘብ ቢተመኑ ኖሮ ብዙ ገንዘብ የሚያስወጡ ይሆኑ እንደነበር አስረድተዋል::

የስፖርት ክሊኒኩ መከፈትንም ተከትሎ ከብሄራዊ ቡድን ተጫዋቾች አልፎ ሌሎች ተጫዋቾች የሚታከሙበትን ሁኔታ የሚመቻች መሆኑ ተገልጿል:: ስምምነቱ ለ4 አመት የሚዘልቅ መሆኑ ተነግሯል::

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here