ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት መ/ቤቶች ንብረት ያላግባብ በሀላፊዎች እጅ እንደሚገኝ በኦዲት መረጋገጡ ተነግሯል፡፡
የኦዲት ምርመራው 13 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት በሀላፊዎች እጅ እንደሚገኝ በምርመራው ማሳየቱም ነው የተጠቆመው፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 269 ተቋማት ላይ በተደረገ የንብረት ቆጠራ ወደ 24 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት በጉድለት ተገኝቷል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር_ባለስልጣን የህንፃና ንብረት ኦዲት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ምሩጽ ታዬ በተቋማቶች ላይ ከተገኘው ጉድለት ውስጥ ወደ 10 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲመለስ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም በተቋማቱ ከተመዘገበው ንብረት ላይ ጉድለት የተገኘባቸው ሃላፊዎች ከስራ ገበታ እንዲባረሩ እና በህግ እንዲጠየቁ አድርገናል ብለዋል፡፡



