ቅዳሜ ነሐሴ 25 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት አለባቸው ሲሉ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳስበዋል።
የ33ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ” ፍትሃዊ እና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም ! ” በሚል ጭብት ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ተካሒዷል።
ጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ፥ በትምህርት ዘርፍ ላይ ያሉ አመራሮች የትምህርት ሥራን ከፖለቲካ መለየት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
” ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የመላው ኢትዮጵያውያን እንጂ የተቋቋሙበት መንደር አይደሉም ” ብለዋል ሚኒስትሩ።
” ከዚህ በኋላ በምንም ዓይነት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በአካባቢ የሚመደብበት ሁኔታ እንደማይኖር ” ገልፀዋል።
” የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምደባ በውድድር እና በብቃት ላይ ብቻ የተመሠረተ እንዲሆን ይሠራል ” ሲሉም አስታውቀዋል።



