የትግራይ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር የሕግ አማካሪ ዘርአይ ወልደሰንበት ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸው ተገለጸ

0
971

ከ1/09/2011 ጀምሮ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የትግራይ ክልል መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር የሕግ አማካሪ ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩት ዘርኣይ ወልደሰንበት ‹‹መገፋት እና በደል እየደረሰብኝ›› ነው በሚል ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን አስታወቁ።

ዘርኣይ ለትግራይ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዘዳንት ባስገቡት መልቀቂያ ደብዳቤ ላይ በክልሉ ተመድበው በሚሰሩበት የኃላፊነት ስፍራ ላይ እጅግ እልህ አስጨራሽ እና እንግዳ በሆነ ስራ ሁኔታ ውስጥ ማለፋቸውን ጠቁመው ‹‹በማይሻሻልአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ መቀጠል ከዚህ በኋላ ትርፉ ቀን ተቀን ንዴት›› እንደሆነ ጠቁመዋል። በመሆኑም አማካሪው ከጥር 1/2012 ጀምሮ በአስገዳጅ ሁኔታ ከኃላፊነታቸው የለቀቁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ዘርኣይ ወልደ ሰንበት በፌደራ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኝነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ወደ ትግራይ ክልል በማቅናትም በባለፈው ዓመት ግንቦት 1/2011 ጀምሮ የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሕግ አማካሪ ሆነው መመደባቸው የሚታወስ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here