‹‹ከ 1ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም›› የትምህርት ሚኒስቴር

ሰኞ ጳጉሜ 04 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ)የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በአጠቃላይ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ሲሆን በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ 4 ትምህርት ቤቶች ከሀረሪ ክልል ውጭ ሁሉም ክልሎች ላይ አንድም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን አመላክተዋል።

በአጠቃላይ ከፍተኛ ውጤት ከ500 በላይ ያመጡ ተማሪዎች ባለፈው አመት 273 የነበሩ ሲሆን በአሁኑ 1ሺ 220 ተማሪዎች ከ500 በላይ ያመጡ ናቸው ተብሏል።

እንዲሁም በዘንድሮ 12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 5 ነጥብ 4 በመቶ ፈተናውን አልፈዋል ይህም ማለት 36 ሺ 4 መቶ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ማለፊያ ነጥብ አስመዝግበዋል፡፡

ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት ሴቶች ሲሆኑ በተፈጥሮ ሳይንስ ካቴድራል ትምህርት ቤት 575ከ 600 እና በማህበራዊ ሳይንስ ኢትዮ ፓረንትስ ትምህርት ቤት 538 ማስመዝገባቸው ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 21 በመቶ (ከ10ሺ በላይ) ተማሪዎችን ከክልሎች ደግሞ ሀረር 337 እና ኦሮሚያ 8ሺ በላይ ተማሪዎች ማለፋቸውን እንዲሁም ሁሉም ክልሎች ከአምናው የተሻለ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

በዘንድሮ አመትም የሬሜዲኣል ፈተና የሚኖር ሲሆን የተፈታኞች ቁጥር ግን ከአምናው ቁጥር እንደሚቀንስ በመግለቻው ተጠቅሷል

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here