ክልሉ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ892 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

0
256

ማክሰኞ ጳጉሜ 05 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የይቅርታ አዋጁን መስፈርት ላሟሉ 892 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስትዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ እንደገለጹት፤ ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ሥነ-ምግባር ያሳዩ እና በሕግ በተደነገገው የይቅርታ መስፈርትን ማሟላታቸው በክልሉ የይቅርታ ቦርድ ተጣርቶ የቀረቡ ናቸው።

የህግ ታራሚዎቹ በመደበኛ የይቅርታ ሕግ እና ሌሎች ተጨማሪ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተብለዉ በልዩ ሁኔታ የቀረቡ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ይቅርታው ከተደረገላቸው 892 የህግ ታራሚዎች መካከል 879 ከእስር የሚፈቱ ሲሆን ቀሪ 13 ታራሚዎች የእስራት ጊዜያቸው የተቀነሰላቸው መሆኑን ርዕሰ መስትዳድሩ ጨምረው ገልጸዋል።

የይቅርታ ተጠቃሚ ከሆኑት የህግ ታራሚዎች መካከል 831 ወንዶች ሲሆኑ 48 ደግሞ ሴቶች መሆናቸውንም አመልክተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here