የደብረፅዮን (ዶ/ር )ቡድን መፈንቅለ መንግስት ሊያደርግብኝ ነው ሲል የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን አስታወቀ  

0
578

ረቡዕ መስከረም 08 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የደብረፅዮን ቡድን ለስልጣኑ ሲል የትግራይ ህዝብ ላይ ተደጋጋሚ ክህደት እየፈፀመ ይገኛል ሲል የጌታቸው ረዳ ቡድን ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።

አባላቱ አክለውም የትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ጄኖሳይድ ለስልጣኑ ሲል ወደ መካድ ደርሷል ሲል ከሰዋል።

 

የጌታቸው ቡድን መግለጫው የደብረፅዮን(ዶ/ር) ቡድን ማንኛውም አካል ላይ ውሳኔ የማሳለፍ ሆነ እርምጃ የመውሰድ ፖለቲካዊ፣ ሞራላዊ እና ህጋዊ ስልጣን እንደሌለው ለህዝባችን እና ለአባላቶቻችን ማሳወቅ እንወዳለን ብሏል።

የአቶ ጌታቸው ቡድን ከፌደራል መንግስት ጋር የህወሓት ህጋዊ ሰውነትን ለመመለስ በምናደርገው ፓለቲካዊ ድርድር መላው አባላችን እና ደጋፊ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን ማለታቸውን አዲስ ማለዳ ከመግለጫው ተመልክታለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here