ጋዜጠኞቹ ከሀገር መሰደዳቸውን አስታወቁ

0
528

ረቡዕ መስከረም 08 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከሶስት ወራት በፊት ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው እና በላይ ማናዬ፤ ሀገራቸውን ለቅቀው ለመሰደድ መገደዳቸውን ተናገሩ።

ሁለቱ ጋዜጠኞቹ የተሰደዱት፤ በመንግስት የጸጥታ አባላት በተሰጣቸው “ለህይወታቸው የሚያሰጋ” “ማስጠንቀቂያ” እና ከእስር ከተፈቱ በኋላ በሚደረግባቸው “ክትትል” ምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ በላይ እና በቃሉ 11 ቀናት የፈጀ “አስቸጋሪ ጉዞ” በማድረግ ከሀገር የወጡ ሲሆን ይህም ባለፈው ሳምንት ሰኞ ጳጉሜ 4፤ 2016 መሆኑን አስረድተዋል።

ሆኖም ጋዜጠኞቹ በአሁኑ ወቅት ያሉበትን ሀገር፤ “ከደህንነት ስጋት” ጋር በተያያዘ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ሁለቱ ጋዜጠኞች ለእስር ተዳርገው የነበረው፤ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ባበቃው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ነበር።

በአማራ ክልል እና እንዳስፈላጊነቱ ደግሞ “በየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ” ተፈጻሚነት የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ የተላለፈው ሐምሌ 28፤ 2015 ነበር።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here