👉🏿 ኢትዮጵያ በፓኪስታን የደረሰውን የሽብር ጥቃት አወገዛለች
ሰኞ፣ መስከረም 13 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በፓኪስታን በከይበር ፓክቱንክዋ ግዛት የዲፕሎማቲክ ኮንቮይ ላይ የሽብር ጥቃት ተፈፅሟል፡፡
የዲፕሎማቲክ ኮንቮዩ የኢትዮጵያ አምባሳደርን ጨምሮ፣ ሩዋንዳ፣ ዚምባብዌ፣የኢንዶኔሲያ እና የሌሎች ሃገራት አምባሳደሮችን አካቷል ተብሏል፡፡
እንዚህ ከ11 አገራት የተውጣጡ ዲፕሎማቶች በደረሰው የሽብር ጥቃት ጉዳት ባይደርስባቸውም የአንድ ፖሊስ ህይወት ሲቀጥፍ ሶስት ፖሊሶችን አቁስሏል፡፡
ኢትዮጵያ በበኩሏ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል አውግዛ ዲፕሎማቶቹን ሲያጅብ ለነበረው የሟች ፖሊስ ቤተሰብም መጽናናትን ተመኝታለች፡፡
የሽብር ጥቃቱን በጽኑ ያወገዘችው ኢትዮጵያ÷ ለፓኪስታን ሕዝብና መንግሥትም መጽናናትን መመኘቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡



