የወጣውን የሴት ባክ ህግ በመጣስ የሚሰራ ግንባታን ሽፋን የሚሰጡ ተቆጣጣሪዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

0
403

ማክሰኞ መስከረም 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ በሚከናወኑ ግንባታዎች ላይ የወጣውን የሴት ባክ ህግ ወይም ህንጻዎች ከመንገድ መራቅ ያለባቸው እርቀት እና የመሬት ስፋትን ያላገናዘበ ግንባታ ለማከናወን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ይህን ያስታወቀው ለአስራ አንዱም ክ/ከተማ ግንባታ ፈቃድ እና ቁጥጥር ጽ/ቤት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ካቢኔ በሰኔ 10 ቀን 2016 በሶስተኛ መደበኛ ስብሰባው ወቅት ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል ህንጻዎች ከመንገድ መራቅ ያለባቸው እርቀት መሆኑ ይታወቃል፡፡

ውሳኔው ተግባራዊ እንደሚደረግ ከዚህ ቀደም የተገለጸ ቢሆንም አንዳንድ አስፈላጊውን የዲዛይን ማሻሻያ ሳያደርጉ እና የግንባታ ማስጀመሪያና የእርከን ማስታወቂያ ሳይወስዱ የወጣውን ህግ በመጣስ ወደ ግንባታ ለመገንባት የሚሞክሩ አልሚዎች መኖራቸው ተመላክቷል፡፡

እንዲሁም ይህን መሰል ድርጊት በየደረጃው ያሉ ስነምግባር የጎደላቸው አመራሮች እና ባለሙያዎች በሚሰጡት ሽፋን ጭምር የሚከናወን እንደሆነ ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ባለስልጣኑ የግንባታ ማሻሻያውን ፈቃድ ሳይውስዱ እና የግንባታ ክትትልና ቁጥጥር ሳያድርጉ መገንባታ ማድረግ በምንም መልኩ ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ መሆኑን አሳስቧል ፡፡

በተጨማሪም ህግ በመጣስ ግንባታ የሚያከናውኑ በክፍለ ከተማቸው እና በወረዳቸው የግንባታ ስራን ባግባቡ የማይከታተሉ እና የማይቆጣጠሩ ህገወጦችን አይቶ እንዳላየ በማለፍ ሽፋን በሚሰጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች ላይ ባለስልጣኑ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here