በእነ ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ላይ የተሰጠው እግድ እንዲጸና ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጠ

0
368

ረቡዕ መስከረም 22 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በመስከረም 08 ቀን 2017 ዓ.ም የተሰጠው እግድ ሊነሳ አይገባም በማለት የእነ ዶር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እግዱ እንዲፀና ትእዛዝ መስጠቱ ተገልጻል፡፡

የእግድ መጣስ መኖር አለመኖር ጋር ተያይዞ የቀረበውን ክርክር የመደበኛ ችሎት ጊዜ ሲጀምር ይታያል ሲል ለጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀሮ ሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የተላለፉ ውሳኔዎችና ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ያካሄደው የኦሊምፒክ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ እንዲታገድ በቀረበው የፍትሐብሔር ክስ መሠረት በፍርድ ቤት ዕግድ መሰጠቱ የሚታወስ ነው፡፡

ተከሳሾቹ በዋናነት የቀረበባቸው ክስ የፍትሐብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 154 እና 205 ድንጋጌዎችን በመተላለፍ፣ የኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ኮሚቴን ጠቅላላ ጉባዔ በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፋቸውና ሕገወጥ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ምርጫ አካሄደዋል በሚል ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here