ሐሙስ መስከረም 23 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአካታች ፋይናንስና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ከሚሠራው InFTF ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን፣ በሀገሪቱ ብሎም በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን፣ በብሎክ ቼን ቴክኖሎጂ የታገዘ የሬሚታንስ አገልግሎት በጋራ ለማስጀመር ተስማምተዋል፡፡
ባንኩ ያደረገው ስምምነት በሬሚታንስ ዘርፍ ያሉትን ችግሮች የሚቀርፍ አገልግሎትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል።
የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች አነስተኛ ከሆነ የገንዘብ መጠን ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ፈንድ በተመጣጣኝ ክፍያ ከ3 ሰከንድ ባልበለጠ ጊዜ፣ ለተጠቃሚው የሚደርስ ፈጣን የሬሚታንስ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል፡፡



