ቅዳሜ ጥቅምት 02 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሐምሌ 22/2016ዓ.ም እስከ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ድረስ በአራት ዙር ከ282 ሚሊዮን 459 ሺሕ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለተለያዩ የውጭ ምንዛሬ ፈላጊ ደንበኞች መደልደሉን አስታውቋል፡፡
የውጭ ምንዛሪ ፍቃድ ከተሠጣቸው ደንበኞች መካከል ፋብሪካዎች፣ የገቢ እና ወጪ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ መድኃኒት አምራቾች፣ አገልግሎት ሰጪዎች፣ የመንግስትና ሕዝብ ተቋማት እና በውጭ ኢንቨስትመንት የተቋቋሙ ድርጅቶች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
ለአብነት ለፋብሪካ ጥሬ እቃ እና ለተጠቃሚ የሚቀርቡ የተለያዩ የምግብ፤ መድኃኒት እና መገልገያ ቁሣቁሶች መግዣ ከ208,290 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር እንዲሁም ለማሽነሪዎች መግዣ 42,777 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር መደልደሉን ባንኩ ገልጿል።
ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ለደንበኞች በመስጠት የውጪ ገቢ ንግድ የተቀላጠፈ እንዲሆን አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡



