ዓርብ ጥቅምት 8 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል፡፡
በዚህም የፍህ ሚኒስትር የነበሩትን ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዮስን የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትር አድረገው ሾመዋል፡፡
በተጨማሪም ቀደም ሲል የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አግልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ የነበሩትን ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ን የቱርዝም ሚንስቴር ሚንስትር አድርገው የሾሙ ሲሆን ፤ ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴን ደግሞ የፍትህ ሚንስቴር ሚንስትር በማድረግ ሹመት ሰጥተዋል፡፡



