በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ የተከሰተውን የእሳት አደጋ እስከ አሁን መቆጣጠር ባለመቻሉ በሄሊኮፕተር እየተሞከረ መሆኑ ተገለጸ

0
334

👉 “በመርካቶ ሸማ ተራ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ለደረሰው ጉዳት እጅግ አዝነናል” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር ከእሳት አደጋ  እና ስጋት መከላከል እንዲሁም  ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን ርብርብ እየተደረገ  ስለመሆኑ የገለጹት ከንቲባዋ አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት  አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው ብለዋል።

በመሆኑም የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን  ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከንቲባዋ አክለውም ይህንን አደጋ ለመቀነስ ርብርብ እያደረጉ የሚገኙትን አካላት ሁሉ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here