ረዕቡ ህዳር 25 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት በላሊበላ ከተማ 45 ሆቴሎች ሙሉ በሙሉ ስራ ማቆማቸውን የላሊበላ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በተመሳሳይ በጦርነቱ ምክንያት ወደ ስፍራው የሚመጡ ቱሪስቶችን ማጣቱን እና በዚህም 200 የሚደርሱ የላሊበላና አካባቢዉ አስጎብኝዎች ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር መዳረጋቸዉን የላሊበላ ከተማ አስጎብኝ ማኅበር ማስታወቁን ዶችቬለ ዘግቧል፡፡
ባለፉት አራት አመታት ያጋጠመው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ባለፉት ሁለት ዓመታት ደግሞ በአካባቢዉ በመንግስትና በፋኖ ታጣቂ ኃይሎች መካከል ባለ ግጭት ቱሪስቶች ወደ አካባቢዉ እነዳይመጡ ማድረጉ ተጠቁሟል።



