የንግድ ውድደር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ማሻሻያ ሊደረግበት ነው

0
861

የንግድ ውድድ እና ሽማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ሲመራበት የነበረው አዋጅ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እና የባለስልጣኑን አስተዳደራዊ ስልጣን ለመወሰን የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃን በሚመለከት በሚፈጸሙ የሕግ ጥሰቶች ላይ አስተዳደራዊ እና የወንጀል ጉዳዮችን የመመርመር እና የመክሰስ ተግባራት ሲያከናውን የነበረ ሲሆን ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ አንደ አዲስ ሲቋቋም የወንጀል ክስ ስልጣኑን መውሰዱን ተከትሎ አዋጁን ማሻሻል እንዳስፈለገ ታውቋል።

በባለሥልጣኑ ይከናወን የነበረው የዓቃቤ ህግነት እና የወንጀል ምርመራ ተግባር ወደ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ እንዲሁም የወንጀል ምርመራው ወደ ፌደራል ፖሊስ እንዲሄድ በመደረጉ ምክንያት ባለሥልጣኑ ከፀረ ንግድ ውድድር ተግባራት እና ከሸማቾች ጥበቃ ጋር በተያያዘ ሊኖረው የሚገባውን አስተዳደራዊ ሥልጣን በህግ ለመወሰን ሲባል አዋጁን ማሻሻል እንዳስፈለገ ተገልጿል።

እንዲሁም የሌሎች አገራት ልምድ መሠረት በማድረግ የነበሩትን ክፍተቶች በመሙላት አዋጁ ከህገ መንግስቱ እና ኢትዮጵያ ከፈረመችባቸው ዓለም አቀፍ ህጎች እና ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር የተጣጣመ እና ሊያሰራ የሚችል አዋጅ ማውጣት በማስፈለጉ አዋጁን በተሻሻለ አዋጅ ለመተካት የተደረጉ ዝርዝር ማሻሻያዎች እንደተደረጉ ባለስልጣኑ ገልጿል። ማሻሸያው ሲደረግም ከአገር ውስጥ ህጎች፣ ከንግድ ፈቃድ እና ምዝገባ አዋጅ ፣ ከንግድ ህግ፣ ፍትሀ ብሄር እና ወንጀል ህግ፣ ከብሮድካሰት አዋጅ፣ ከምግብ እና መድሂት ቁጥጥር አዋጅ፣ ከአእምሮአዊ ንብረት ጥበቃ አዋጅ ጋር የማጣጣም ስራ ተከናውኗል።

በተጨማሪም ከውጪ ሀገር ህጎች የተባበሩት መንግስታት የሸማቾች መመሪያ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የደቡብ አፍሪካ፣ህንድ፣ ብራዚል፣ አወስትራሊያ፣ ዛምቢያ እና የኬንያ የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ህጎችን ልምዶችንና ሰነዶችን ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ለማስመማት እንደተሞከረ ተገልጿል። የባልሰስልጣኑ ከፍተኛ የህግ በ ለሙያ በቀለ ሀብተ ማርያም በአዋጅ ማሻሻያው ባለስልጣኑ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን መመልከት የሚያስችል ስልጣን ይሰጠዋል ያሉ ሲሆን እነዚህን አስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚያይ አስተዳደራዊ ችሎት እና በባለስልጣኑ የቢሮ እና መሰል ድጋፍ የሚደረግለት ገለልተኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት እንዲኖረው ያደርጋል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አሻሚ ቃላት እንዲሁም የቃላት ትርጓሜ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ያሉት በቀለ በቀድሞው አዋጅ መሰረት “ማንኛውም ነጋዴ በውህደት ስምምነት ወይም ቅንብር ለመሳተፍ ሲያቅድ የታቀደውን ውህደት በዝርዝር በመግለጽ ለባለሥልጣኑ የውህደት ማስታወቂያ ማቅረብ አለበት ”በሚለው ላይ የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ማለትም “ሲያቅድ” ብቻ የነበረው በአዲሱ ረቂቅ ህግ ላይ ሲያቅድ ወይም “ሲወስን” በሚል እንዲስተካከል ተደርጓል ብለዋል።

ለ“ንግድዕቃዎች” ተሰጥቶ የነበረው ትርጉም ለሚንቀሳቀሱ ንብረቶች ብቻ በመሆኑ እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ወይም የንግድ እቃዎች ላይ የሚፈጸመውን ግብይት የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ይጨምራል በሚል የተስተካከለ ሲሆን በቀድሞው አዋጅ ሸማች ተብለው የተገለፁ ለግል ፍጆታ ከሚገዙ ግለሰቦች በተጨማሪ ለራሳቸው ፍጆታ እና ለትርፍ ላልሆነ ዓላማ የሚሸምቱ ተቋማትም እንዲካተቱበት ተደርጓል።

እነዚህን እና መሰል ዝርዝር ጉዳዮች በአዋጅ ማሻሻያው ረቂቅ ላይ የተካተቱ ሲሆን በማሻሻያው ላይ የክልል እና የመስሪያ ቤቱ የስራ ሀላፊዎች አስተያት እንዲሰጡበት በማድረግ በንግድ ሚኒስቴር የማስገምግም ስራዎች በማከናወን ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት መላኩን ባለሙያው ተናግረዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 64 ጥር 16 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here