መዝገብ

Author: በለጠ ሙሉጌታ

የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ሥልጠና በመንግሥት ወጪ መደረጉ ቅሬታ አስነሳ

የመንግሥት ተንቀሳቃሽ ሂሳቦች ዝግ ሆነው ቆይተዋል ብልፅግና ፓርቲ ከመስተዳድር ጀምሮ እስከ ዞን ላሉ የቢሮ ኃላፊዎች እና ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ እየሰጠ ላለው ሥልጠና የውሎ አበልን ጨምሮ ሌሎች ወጪዎችን ከመንግሥት ካዝና እንዲሸፈን መደረጉ ቅሬታ አስነሳ። ለፓርቲው አባላት እና ከክልላዊ መስተዳደር…

ብሔራዊ ባንክ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ አደረገ

ጭማሪው የሰራተኞችን የስራ ደረጃ መሰረት ባደረገ መልኩ የተደረገ ነው ብሔራዊ ባንክ ከጥር 01/2012 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ ለሠራተኞቹ አደረገ። ባንኩ ከ50 በመቶ እስከ 230 በመቶ የሚደርስ የደሞዝ ጭማሪ ተግባራዊ ማድረጉን ለሠራተኞቹ በላከው የውስጥ ደብዳቤ ላይ…

የታኅሳስ ወር የቡና ወጪ ንግድ ቅናሽ ተመዝግቦበታል

በታኅሳስ ወር ወደ ውጪ አገራት የተላከው የቡና መጠን ቢጨምርም የተሰበሰበው ገንዘብ መጠን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ4 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ማሳየቱ ተገለፀ። ባሳለፍነው ወር ቡናን ወደ ውጪ አገራት በመላክ 14 ሚሊዮን ዶላር ማግኘት መቻሉ የተገለፀ ሲሆን፣ የወሩ የቡና…

ንግድ እና ኢንዱስተሪ ሚኒስቴር ለ 20 ዓመታት የተገለገለበትን ሕንፃ ሊለቅ ነው

ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከልማት ባንክ በመከራየት ከ20 ዓመታት በላይ ሲገለገልበት ከነበረው እና በባንኩ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ባለ ስምንት ወለል ሕንጻ ሊለቅ እንደሆነ አስታወቀ። ባንኩ አገልግሎቶችን ለደንበኞች አመቺ በሆነ መልኩ ለመስጠት የቦታ ጥበት እንደገጠመው የገለጸ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በተለያዩ…

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ8 ሺሕ በላይ አዲስ ተመራቂዎችን ሊቀጥር ነው

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በሚገኙ ከማእከላት እስከ ወረዳ ባሉ ክፍት የሥራ ቦታዎች 8 ሺሕ 100 አዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን በመቅጠር ሂደት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ። በ2010 እና 2011 ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከ56 በላይ በሚሆኑ የትምህርት መስኮች የተመረቁ የአዲስ አበባ ወጣቶች እንዲወዳደሩ ጥሪ…

በአዲስ አበባ ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው ሼዶች ያለሥራ ቆመዋል

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የወጣባቸው 527 ሼዶች የኤሌክትሪክ ኃይል ባለማግኘታቸው ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ አለመቻሉን አስታወቀ። የመሥሪያ ቦታዎቹ በአዲስ አበባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንደሚገኙ የገለፀው ኤጀንሲው፣ ግንባታቸው ከተጠናቀቀ ከኹለት…

የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ባለንብረቶችን መብት የሚገድብ ሕግ ተረቀቀ

አዋጁ ክልሎች የራሳቸውን ቁራሽ የከተማ መሬት የሚያስተዳድሩበት መመሪያ ማዘጋጀት እንዲችሉ ዕድል ይሰጣል የመሬት ባለይዞታዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዲይዙ የሚያስገድድ እና ይህንን በማያደርጉ ባለይዞታዎች ላይም መብቶቻቸውን የሚገድብ የአዋጅ ማሻሻያ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ። የፌዴራል የመሬት እና መሬት ነክ ይዞታ ምዝገባ መረጃ…

የወሃ ናሙናን ወደ ውጪ መላክ የሚያስቀር የምርምር ማእከል ተገነባ

የውሃን ኬሚካላዊ ይዘት ለማረጋገጥ ወደ ውጪ አገር መላክን የሚያስቀር የመስኖ እና ውሃ አስተዳደር ምርምር ማእከል ተገነባ። ማእከሉ የተገነባው ከሞሮኮ ንጉሥ መሐመድ 6ኛ የዘላቂ ልማት ፋውንዴሽን በተገኘ 140 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እና በመንግሥት 150 ሚሊዮን ብር በጀት ነው። ከከርሰ ምድር ተቆፍሮ…

ኢትዮጵያ፡ ከድሃም ደሃ

ኻያ ብር ብቻ በአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ምን ምን ሊያደርግለት ይችላል? የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ምክንያቶች ይህ ብር ለአንድ ሰው የእለት ወጪ ሊሸፍን እንደሚችል አድርጎ የተናገረበት አንድ ወቅት ነበር። በዚህም ከድህነት ወለል በታች የሚኖሩ ዜጎች ብዛት ከ23 በመቶ እንደማይዘል ተደርጎ…

ኢሕአዴግ መፍረሱን ለምርጫ ቦርድ አሳወቀ

ኢሕአዴግ የግንባሩ ሶስት ፓርቲዎች ከስመው መውጣታቸውን እና ብልጽግና የተሰኘውን አዲስ ፓርቲ ማቋቋማቸውን ተከትሎ ግንባሩ አለመኖሩን በመግልፅ መፍረሱን የሚያሳውቅ ደብዳቤ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላከ። ከ 15 ቀናት በፊት ለቦርዱ በላከው ደብዳቤም ግንባሩን ከመሰረቱት ሶስቱ ፓርቲዎች ወደ ብልፅግና ፓርቲ መግባታቸውን ተከትሎ አንዱ…

በአዲስ አበባ አንድ ሚሊዮን ነዋሪዎች የጤና መድህን አባል ሆኑ

በአዲስ አባባ ከተማ በሶስት ወራት ውስጥ በስራቸው ከአምስት ሰው በላይ የያዙ ከ183 ሺሕ በላይ አባ ወራዎች የማህበረሰብ አቀፍ ለጤና መድሕን አባልነት ተመዝግበው ከ 75 ሚሊዮን ብር በላይ ማዋጣታቸውን መሰብሰብ መቻሉን የኢትጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ አስታወቀ። ምዝገባው ከ ጥቅምት ወር ጀምሮ…

የንግድ ውድደር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ማሻሻያ ሊደረግበት ነው

የንግድ ውድድ እና ሽማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ሲመራበት የነበረው አዋጅ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እና የባለስልጣኑን አስተዳደራዊ ስልጣን ለመወሰን የሚያስችል የአዋጅ ማሻሻያ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታወቀ። ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 813/2006 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የንግድ ውድድር እና የሸማቾች ጥበቃን በሚመለከት በሚፈጸሙ የሕግ…

ከ19 የፖለቲካ ፓርቲዎች አገራዊ ጥምረት ሊፈፅሙ ነው

ከ19 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያቀፈ ‹‹ትብብር ለህብረ ብሔር ፌደራሊዝም›› የሚል ስያሜ የሚሰባሰብ ቅንጅት በመመስረት ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡ የአራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ትብብር ለህብረ ብሔር ፌደራሊዝም የሚል ስያሜ የተሰጠው ጥምረት ለመመስረት የጥምረት ጥያቄያቸውን ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊ ሰነዶችን በሟሟለት ማቅረባቸውን ለአዲስ ማለዳ…

ተቋርጦ የነበረው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሥም ማዘዋወር በከፊል ተጀመረ

የአዲስ አባባ ከተማ መሬት እና መሬት ነክ ይዞታ ማረጋገጫ በመዝገብ ተመዝግበው የነበሩ ቤቶችን በዘመናዊ መልክ በመረጃ ቋት ለመመዝገብ ከታኅሳስ 6/2012 ጀምሮ አቋርጦት የነበረውን ሥም ማዘዋወርን ጨምሮ ሌሎችከይዞታ ባለቤትነት ጋር የተያያዙ አገልግሎቶችን መጀመሩን አስታወቀ።  የጋራ መኖሪያ ቤቶች አመዘጋገብ ስርዓት በወረቀት በመመዝገብ…

መገናኛ ብዙኀን የቅድመ ምርጫ ትንበያ እንዲያዘጋጁ የሚፈቅድ መመሪያ ተዘጋጀ

በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተረቀቀው የመገናኛ ብዙኀን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የሥነ ምግባር እና አሠራር መመሪያ፣ መገናኛ ብዙኀን የቅድመ ምርጫ ትንበያ በማዘጋጀት ለመራጩ ሕዝብ ማቅረብ እንዲችሉ ደነገገ። መገናኛ ብዘኀኑ የሕዝብ አስተያየት አሰባስበው ትንበያውን በራሳቸውም ይሁን በሌሎች ድርጅቶች ካከናወኑ፣ የድርጅቶቹን ሥም በመግለፅ…

የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት 23 በመቶ ደረሰ

ግሽበቱ ካለፈው ዓመት የአስር በመቶ ጭማሪ አሳይቷል የትግራይ ክልል የምግብ ዋጋ ግሽበት ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር እስከ አስር በመቶ የሚደረስ ጭማሪ ማስመዝገቡን የብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ዘገባ አመላከተ። ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ግብዓቶች ላይ በክልሉ የተስተዋለው የግሽበት መጠን በ2011 ከነበረበት…

ለሰዎች እና ለእንስሳት ምግብ የሚሆኑ 23 የቀርከሃ ዝርያዎችን ማባዛት ተጀመረ

የኢትዮጵያ የአካባቢ እና ደን ልማት ኢንስቲትዩት 21 አዳዲስ የቀርከሃ ዝርያዎችን ከኤስያ እና ከደቡብ አሜሪካ በማስገባት ለሰዎች ምግብ እንዲሁም ለእንስሳትን መኖ እስከ 65 በመቶ ለመሸፈን ሥራ ጀመረ። ከ 800 እስከ 1 ሺሕ 800 ሜትር ከፍታ መሀል ባለው ክፍተት መብቀል የሚችሉት ዝርያዎቹ፣…

ግዙፍ የቻይና የጨርቃ ጨርቅ አምራች በኢትዮጵያ ሥራ ሊጀምር ነው

‹ሸንቴክስ› የተሰኘ ግዙፉ የቻይና የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት አምራች ድርጅት በቦሌ ለሚ ኹለት ኢንዱስትሪያል ፓርክ ለማምረት የሚያስችለውን የኪራይ ውል መፈራረሙ ተገለፀ። በቻይና ኹለተኛው ግዙፍ የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት አምራች የሆነው ድርጅቱ፣ በኢትዮጵያ ከ 65 ሚሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ…

ለኹለት ዓመት በሶማሌ ክልል የቆየው የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ለአዲስ አበባ ተሰጠ

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ከሶማሌ ክልል ተከስተው በነበሩ የጸጥታ ችግሮች የታሰበውን ያህል መንቀሳቀስ አለመቻሉን ተከትሎ ክልሉ ዋንጫውን ለአዲስ አበባ ማስረከቡ ተገለፀ። ዋንጫው ባለፉት ኹለት ዓመታት በሶማሌ ክልላዊ መንግሥት ስር የቆየ ሲሆን፣ በክልሉ በነበሩ ተደጋጋሚ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች የታሰበውን ያህል መንቀሳቀስ…

ኢትዮጵያ አዲስ የካንሰር ሕክምና መሣሪያ ልታስገባ ነው

ከዓለማቀፉ የአውቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ በተገኘ ድጋፍ ‹ሳይክሎትሮን› የተሰኘ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነ የካንሰር ምርመራ እንዲሁም ሕክምና ለማድረግ የሚያስችል መሣሪያ ለመግዛት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ። በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው መሣሪያው፣ የካንሰር ምርመራን ለማከናወን ከማገዙም በላይ የካንሰር ሕክምና እንዲሁም የኩላሊት ንቅለ ተከላ ያደረጉ ግለሰቦችን…

ለሴቶች ምቹ ያልሆነችዋ አዲስ አበባ

መዲናችን አዲስ አበባ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የሚከናወንባት፣ በርካታ ግዙፍ የመንግሥት እና ዓለማቀፋዊ የንግድ ተቋማትን በውስጧ አቅፋ የያዘች ሰፊ ከተማ ነች። የከተማዋ የዳቦ ቅርጫትነት፣ የሕንጻዎቿ ውበት እና የመብራቷ ድምቀት ተረክ ሆዱን እያባባው መዳረሻውን አዲስ አበባ ላይ የሚያደርገው ሰው እያየለ መሔድ የከተማዋ…

ከኹለት ወራት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የመጅሊስ ምርጫ ይካሄዳል ተባለ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሸማጋይነት መደበኛ ምርጫ እስኪካሄድ የተዋቀረው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (መጅሊስ) ቦርድ ከኹለት ወር ባነሰ ጊዜ ቋሚ የመጅሊስ ምርጫ ለማካሄድ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ። በሚያዚያ 23/2011 የተቋቋመው የሽግግር ጉባኤ 26 አባላት ያሉት የባለአደራ የኡለሞች ምክር…

በ11 ቢሊዮን ብር ወጪ አራት የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጀመረ

በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በ2012 በጀት ዓመት ከ 11 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ አራት የመስኖ ግድብ እና ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጀመረ። ግንባታዎቹ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች የሚከናወኑ ሲሆን፣ ከ 33 ሺሕ በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ ተብሏል። ግንባታቸውም…

በድሬዳዋ ከተማ 82 የእምነት ተቋማት የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጣቸው

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን፣ የሙስሊም መስጊዶች እና ለወንጌላዊያን አማኞች ቤተክርስቲያናት ሲገለገሉቸው ለቆዩ 82 የመሬት ይዞታዎች ማረጋገጫ ሰነድ ተሰጠ። ማረጋገጫ ካገኙት መካከልም 66ቱ መስጊዶች ሲሆኑ ዘጠኝ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርስትያናት እንዲሁም ሰባት የወንጌላዊያን አማኞች ናቸው። የማረጋገጫ ሰነዶቹን በአስቸኳይ…

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የጋዜጠኞች የሥራ ማእከል ሊያዘጋጅ ነው

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ላይ ከ30 እስከ 40 የሚሆኑ ጋዜጠኞች ተቀምጠው ሥራቸውን የሚያካሂዱበት፣ አገልገሎት እንዲሁም መረጃ የሚያገኙበትን የሚዲያ ማእከል በጥቂት ወራት ውስጥ አጠናቆ ክፍት እንደሚያደርግ አስታወቀ። እነዚህ ክፍሎች ጋዜጠኞቹ ተቀምጠው ሥራቸውን የሚሠሩባቸው ሲሆኑ፣ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እጅ…

በደንበኛቸው ላይ በወጣ የእስር ትእዛዝ የታሰሩት ጠበቃ ድብደባ ደረሰባቸው

በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ፍርድ ቤት በሚገኝ የአሠሪ እና ሠራተኛ ክርክር ነገረ ፈጅ የሆኑት አብዲ አብርሃም፣ ደንበኛቸው አልፈፀሙትም በተባለ የአፈፃፀም መዝገብ ምክንያት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ እና ነገረ ፈጁ ይታሰሩ በሚል ባዘዘው መሰረት፣ ለሦስት ቀናት ታስረው በፖሊስም ራሳቸውን እስኪስቱ መደብደባቸውን ተናገሩ።…

ንግድ ባንክ የሠራተኞች ማኅበርን ለማፍረስ እየሠራ ነው ተባለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበር አመራሮችን በማንሳት እና ዕድገት በመስጠት ማኅበሩን ለማዳከም እየሠራ መሆኑ ተገለፀ። የማኅበሩን ፕሬዝዳንት ጨምሮ ሌሎች ሦስት የሥራ አስፈፃሚ አባላት የሥራ ዕድገት እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ ከማኅበሩ ነባር አራት አባላት ባልተለመደ መልኩ ያለ ውድድር ዕድገቱን…

በሩብ ዓመቱ ከግል ሠራተኞች የተሰበሰበው የጡረታ መዋጮ በግማሽ ቢሊዮን ጨመረ

የግል ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ በ 2012 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ከኹለት ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር በላይ የጡረታ መዋጮ መሰብሰቡን እና ይህም ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የግማሽ ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን አስታወቀ። በሩብ ዓመቱም ኹለት ነጥብ አራት ቢሊዮን…

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ማስረጃዎችን መስጠት ጀመረ

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለዐስር ዓመታት አቋርጦት የነበረውን ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ለተማሩ እና ዩኒቨርሲቲው የሚጠይቀውን መስፈርት ላሟሉ ተመራቂዎች ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ሰርተፍኬት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። ከ 2002 ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ ተማሪዎች ዋና የትምህርት ማስረጃ መስጠት ማቆሙን ተከትሎ፣ በርካታ…

ኹለተኛ ዙር የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በያዝነው ወር መጨረሻ ይተገበራል

ከ2011 ጀምሮ በአራት ዓመታት ተከፋፍሎ በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ላይ የሚደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ኹለተኛ ዙር ከታኅሳስ ወር መጨረሻ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ። አገልግሎቱ በኢትዮጵያ የነበረው የአገልግሎት ታሪፍ ከ12 ዓመታት በላይ ማሻሻያ ሳይደረግበት የቆየ መሆኑን በማንሳት፣ እንዲሁም እየጨመረ ከመጣው…

This site is protected by wp-copyrightpro.com