ምክር ቤቱ ለ2012 የ27 ነጥብ 89 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት አፀደቀ

0
998

 

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባሳለፍነው ቅዳሜ የካቲት 07/2012  ባካሄደው 79ኛው መደበኛ ስብሰባ  የ2012 በጀት ተጨማሪ 27 ነጥብ 89 ቢሊዮን ብር ሆኖ እንዲፀድቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱ ተገለጸ።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎች ያሳለፈ ሲሆን  በፌደራል መንግስት ተጨማሪ በጀት እና ወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት ማካሄዱን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል፡፡

ኢኮኖሚው አሁን ከገጠሙት ተግዳሮቶች የሚላቀቅበት የፖሊሲ እርምጃዎችን ተግባራዊ ለማድረግ 18 ቢሊዮን ብር፣ ለልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ትግበራ 2 ቢሊዮን ብር፣ ለእኩል ስራ እኩል ደመወዝ አገራዊ ትግበራ 7 ነጥብ 9 ቢሊዮን በድምሩ 27 ነጥብ 89 ቢሊዮን ተጨማሪ በጀት እንዲፀድቅ የገንዘብ ሚኒስቴር ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል።

ምክር ቤቱም በቀረበው ተጨማሪ በጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍም  ወስኗል።

በያዝነው ዓመት 386ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ጸድቆ የነበረ ሲሆን ተጨማሪ በጀቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካጸደቀው  የበጀት ጉድለቱን ወደ 127 ቢለዮን ብር ከፍ ያደርገዋል ተብሎ  ይጠበቃል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here