ጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ የካቲት 10/2012 ማካሄድ ጀመረ።
በጉባዔውም የክልሉ መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘግቧል።
የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እና ሹመቶችም ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ይፀድቃሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን
ጨፌው በመደበኛ ጉባዔው በህግ የበላይነትና የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ ላይ እንደሚመክርም ተገልጿል።



