የ ‹‹ኮፒ፣ ከት እና ፔስት›› ፈጣሪ ሕይወቱ አለፈ

0
1217

 

የ ‹‹ኮፒ፣ ከት እና ፔስት›› ፈጣሪ እንዲሁም የኮምፒውተር ተመራማሪ የነበረው ላሪ ቴስለር በ74 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡

ቴስለር በግኝቱ ኮምፒውተርን በቀላሉ ለመጠቀም የሚያስችሉትን እንደ ‹‹ኮፒ፣ ከት እና ፔስት››ን በመፍጠር ብዙዎች ኮምፒውተርን በቀላሉ ለመጠቅም እንዲቻላቸው አድርጓል፡፡

የኮምፒውትር  ተመራማሪው ‹‹በከት እና ፔስት ›› ፈጣሪነቱ ይታወቅ እንጂ በርካታ የፈጠራ ባለቤት   እንደሆነም ይነገርለታል፡፡

ላሪ ቴስለር በ1945 በኒዎክር የተወለደ ሲሆን ከኮምፒውተር ጋር የተያያዘው ስራውን የጀመረው በ1960ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ በሲሊከን ቫሊ ኩባንያ  ነበር፡፡

የቴስለርን ሕልፈተ ሕይወት የሰሙ የቀድሞ ባልደረቦቹም ኮምፒውተርን ለመጠም ቀላል ስላደረክልን እና  ስለ ሰራኸው ስራ እናመስግንሃለን ብለውታል፡፡

ተመራማሪው ቴስለር  ከሰራባቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መካከል አፕል፣ አማዞን፣ ያሆ እና ሌሎችም ተጠቃሾች ናቸው፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here