ዳሰሳ ዘ ማለዳ (የካቲት 13/2012)

0
1183

በአማራ ክልል ከ720 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአደገኛና መጤ አረም ተያዘ

በአማራ ክልል ከ720 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአደገኛና መጤ አረም መያዙን የአማራ ክልል የእፅዋት ዘርና ሌሎች ግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን አስታወቀ። በክልሉ እንቦጭ አረምን ጨምሮ 12 አደገኛና መጤ አረም መኖሩን የፀረ ተባይ ኬሚካል፣ ማዳበሪያና ቁጥጥር ባለሙያ ሞገስ ዘውዱ ገልጸዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

የመድኃኒቶችን የጎንዮሽ ጉዳትና የአጠቃቀም ችግር ማቃለል የሚያስችሉ ስድስት ማዕከላት ማቋቋሙን የኢትዮጵያ የምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ገለጸ። አንዳንድ ጊዜ መድሃኒቶች በተገቢው መንገድ ካልተወሰዱ የመላመድ ባህሪ ስለሚኖራቸው ፈዋሽነታቸውን በማጣት የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ የተነገረ ሲሆን ማዕከላቱ ለችግሩ የሚሆን መፍትሄ ያቀርባሉ ተብሏል። (ኢዜአ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

በኢትዮጵያ በሶማሌ ክልል የሚገኘውን የካሉብና ሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ ክምችት ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ግንባታ እስካሁን አለመጀመሩን የማዕድንና ነዳጅ ሚንስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ በዚህ ስፍራ ነዳጅ ማግኘቷን ተከትሎ ነዳጁን ለዓለም ገበያ ለማቅረብ የሚያስችላትን የተፈጥሮ ጋዝ መስመር ዝርጋታ ስምምነት ከጅቡቲ መንግስት ጋር ከአምስት ዓመት በፊት መፈራረሟ ይታወቃል። (ኢትዮ ኤፍ ኤም)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በተማሪ ብዛት 52 በመቶ ድርሻ ቢኖራቸውም አብዛኞቹ የትምህርት ሚኒስቴርን መስፈርት እንደማያሟሉ ተገለጸ። አንድ ሺህ 615 የግል ትምህርት ቤቶች ለመኖሪያ ቤት ታስበው በተሰሩ ቤቶች ተማሪዎችን በተጨናነቀ ሁኔታ እያስተማሩ እንደሚገኙ የትምህርት ስልጠና ጥራት ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ባለሥልጣን ገልጿል። (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

ስድስት የመንግስት ስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ለማዞር እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። የስኳር ፋብሪካዎቹ የጨረታ ሂደት በሚቀጥለው ወር መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሃጂ ኢብሳ ተናግረዋል። በጨረታ ወደ ግል ለማዞር ለሽያጭ የቀረቡት ፋብሪካዎችን ስም ዝርዝር ከመግለፅ ኃላፊው ተቆጥበዋል። (ኢቢሲ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

በአሶሳ ከተማ በዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 46 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከተማው አስተዳደር ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዋና የሥራ ሂደት ባለቤት ዋና ኢንስፔክተር ደረጃ ኢታና አስታወቁ። ግለሰቦቹ በተደራጀ የዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው ተብሏል። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል በሥነ-ምግባርና ሌሎች ችግሮች ከፀረ- ሽምቅ ፣ ከመደበኛ ፖሊስና ከሌሎች የጸጥታ አባልነት የተሰናበቱና የተደራጀ የዘረፋ ቡድኑን በበላይነት ሲመሩ እንደነበር ማስረጃ የተገኘባቸው ናቸው። (ኢዜአ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ነገ ቅዳሜ የካቲት 14/2012 የአንድ  ቀን ነፃ የስራ ዘመቻ ሊያደርግ ነው። በቢሮ እና በመስክ ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች እንደ መደበኛዎቹ የስራ ቀናት ይከናወናሉ ተብሏል ።ደንበኞችም በዕለቱ በመደበኛ የስራ ቀናት የሚሰጡትን አገልግሎቶች በሙሉ ማግኘት እንደሚችሉ ተነግሯል። (የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here