የምጣኔ ሀብት አማካሪ የነበሩት ንዋይ ገ/አብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

0
1304

 

በጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ እና ሀ/ማሪያም ደሳለኝ የሥልጣን ዘመን በምጣኔ ሀብት አማካሪነት ያገለገሉት ንዋይ ገ/አብ  ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ የካቲት 16/2012 ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ከ1970ዎቹ ጀምሮ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በፕላን ኮሚሽን ውስጥ ለረዥም ዓመታት ያገለገሉት ንዋይ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ግንኙነቷ የተጠናከረ እንዲሆን መስራታቸውም ይነገርላቸዋል።

እንዲሁም መሪዎቹ ከአገራት ጋር በሚኖራቸው የፋይናንስ ግንኙነት ለዓመታት አገልግለዋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here