የቀድሞው የጤና ሚኒስትር አሚር አማን (ዶ/ር) መንግስት ከግል የጤና ዘርፍ ጋር በትብብር እና በቅንነት እንዲሰራ በማድረጋቸው ከኢትዮጵያ ጤና ክብካቤ ፌዴሬሽን የተበረከተላቸውን አንድ ሚሊዮን ብር ለኢትዮጵያ ሥራ ፈጠራ ኮሚሽን አበረከቱ።
አሚር ‹‹ይህ የዕውቅና ሽልማት ለአንድ ሰው የተሰጠ ሳይሆን በግሉ ዘርፍና በጤና ሚኒስቴር በኩል ለተጀመረው መልካም ግንኙነት የተሰጠ ነው›› ሲሉ ገልጸዋል።
መንግስት ባለበት የበጀት ውስንነት ምክንያት የጤና ባለሞያዎችን መቅጠር ባለመቻሉ በጊዜያዊነት ስራ አጥተው የተቀመጡ የጤና ባለሞያዎችን ለመደገፍ የተደረገውን ሥራ ያመሰገኑት አሚር ይህ ብቻውን በቂ እንዳልሆነና ሌሎችም ተመሳሳይ ስራዎችን እንዲሰሩ ያበረታታል ብለዋል።


