ቢኒያም ተወልደ እስኪፈቱ እየተጠበቀ ነው

0
665

የቀድሞ የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኀንነት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሌተና ኮሎኔል ቢኒያም ተወልደ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ ከተወሰኑት 63 ሰዎች መካከል ቢሆኑም በመዝገብ ቁጥር ስህተት እስከአሁን አለመፈታታቸው ተገለጸ።

የመዝገብ ቁጠር ስህተቱ ታርሞ ዛሬ የካቲት 18/2012 ለፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ደብዳቤ የተጻፈ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠቀረበት ሰዓት ድረስ ከእስር አለመፈታታቸውን ጠበቃቸው ኃይለ ሥላሴ ገብረ መድሕን ለአዲሰ ማለዳ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በትላንትናው ዕለት 63 ሰዎች ክሳቸው ተቋርጦ እንዲፈቱ ማድረጉም ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here