ልማት ባንክ 71 ድርጅቶች ላይ ምርመራ ማድረግ ጀመረ

0
391

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ብድር ወስደው ያልመለሱ እና የጠፉ 71 ባለሃብቶች እና ሰራተኞቹን በሕግ ለመጠየቅ እንዲሁም ያለአግባብ የባከነ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ግንዘብን ለማስመለስ ምርመራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ።

ምርመራው ሲጠናቀቅ አስተዳደራዊ እና ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ የባንኩ ፕሬዝዳንት ኃይለየሱስ በቀለ ዛሬ ጠዋት በጽህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት ከዚኅ ቀደም ከባንኩ ብድር የወሰዱ 38 ፕሮጅክቶች መውደማቸውንም ኃይለየሱስ ተናግረዋል።

ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉትን ድርጅቶች እና ባላሃበቶች ስም ዝርዘር ከመናገር ግን ተቆጥበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here