ኢትዮ ቴሌኮም ለወራት ሲያካሂድ የቆየውን የማስፋፊያ ስራ በማጠናቀቅ በቪፒኤን አገልግሎት ላይ የ 72 በመቶ ቅናሽን ጨምሮ የፍጥነት እና የዋጋ ማሻሻያዎችን ማድረጉን አስታወቀ።
ቴሌኮሙ ዛሬ በሽራተን አዲስ እያካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ ይፋ እንዳደረገው ከ 12 ሚሊዮን ዶላር ባላይ ወጪ ያደረገበትን ይህንን ማስፋፊያ ከመጪው ሰኞ የካቲት 23 በኋላ ስራ ያስጀምራል። ለብሮድባንድ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ድርጅቶች የ 65 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ያካሄደው ቴሌኮሙ አራት እጥፍ ፍጥነት ያለተጨማሪ ዋጋ ማድረጉንም አስታውቋል። እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬህይወት ታምሩ ገለፃ የብሮድ ባንድ ኢንተርኔት ለመኖሪያ ቤት ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ የ 69 በመቶ የዋጋ ቅናሽ እና ሶስት እጥፍ ፍጥነት መጨመሩን ገልፀዋል።
አገልግሎቱም በመላው አገሪቱ ተደራሽ ይሆና ተብሏል።



