ዳሰሳ ዘ ማለዳ (የካቲት 20/2012)

0
731

የኬኒያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮሮና ቫይረስ ስጋት ከቻይና ወደ ኬኒያ የሚደረገውን በረራ አገደ

የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ አርብ የካቲት 20/2012 በኮሮና ቫይረስ ስጋት ከቻይና ወደ ኬኒያ የሚደረገው የአውሮፕላን በረራ ማገዱ ተገለጸ።

በረራው እንዲታገድም የኬኒያ የህግ ባለሙዎች የበሽታው አሳሳቢነት አስመልክቶ ባሰባሰቡት የጋራ ፊርም እንደሆነም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በኬኒያ እስከ አሁን ድረስ  በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው እንደሌለ ተነግሯል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሰሀራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ለመጀመሪያ ጊዜ በናይጀሪያ አንድ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ ተገኝቷል። (ሮይተርስ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ከዚህ ቀደም አንድ የጥምረቱ አባል የሌላ ጥምረት አባል መሆን አይችልም የሚለውን የመተዳደሪያ ደንቡን አንቀጽ አሻሻለ። ጥር 23/2012 በጠራው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ደንቡን ያሻሻለው መድረክ ለዚህ ውሳኔ መነሻ የጥምረቱ አባላት ይህ አንቀፅ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ እንዳይሰሩ እያገዳቸው መሆኑን በማንሳታቸው ነው ሲሉ የመድረክ ጸሃፊ ደስታ ዲንቃ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ጠቅላላ ጉባኤው በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻ ውሳኔ ማሳለፉን የተናገሩት ደስታ የምርጫ ቦርድ ተወካይም በጉባኤው ተገኝተው መታዘባቸውን ተናግረዋል።(አዲሰ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

የአሜሪካ የአለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ የዩኤስ ኤድ ኢትዮጵያ ለምታካሂዳቸው ምርጫዎች የሚውል ከ 30 ነጥብ አራት ሚሊዮን ዶላር ባለይ ድጋፍ አደረገ፡፡ የድጋፍ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና የዩኤስ ኤድ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ   ዛሬ የካቲት 20/2012 ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርመዋል። ድጋፉ ቀጣዩ ምርጫ ተዓማኒ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ግልፅነት የሰፈነበት እንዲሆን የሚያደርጉ ስራዎች ለማከናወን ይውላል ተብሏል፡፡ (ምርጫ ቦርድ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የአውሮፓ ህብረት የውጪ ግንኙነት እና የደህንነት ፖሊስ ጉዳዮች ተወካይ እና የኮሚሽኑ ምክትል ፕሬዘዳንት ጆሴፍ ቦሬል ዛሬ ጠዋት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ምክክር በነሐሴ ወር ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ህብረቱ ታዛቢዎቹን  እንደሚልክ ይፋ አደረጉ።ጆሴፍ በትዊተር ገፃቸው ይፋ እንዳደረጉትም መጪው ምርጫ ለኢትዮጵያ መረጋጋት እና ዴሞክራሲን ለማምጣት ወሳኝ መለኪያ እደሆነ ገልፀው ህብረቱ ለዐቢይ አህመድ የለውጥ አጀንዳ ያለውን ድጋፍ ያረጋገጠበት ምክክር እንደነበርም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ በተመሰሳይ በግል የትዊተር ገፃቸው ላይ ይፋ እንዳደረጉት ከምክትል ፕሬዘዳንቱ ጋር ‹‹ኢትዮጵያ ስለጀመረችው የብልፅግና ጉዞ እና በቀጠናው ስላሉ መሻሻሎች መክረናል›› ብለዋል።የአውሮፓ ህብረት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ያካሄደቻቸውን አገር አቀፍ ምርጫዎች በተደጋጋሚ መታዘቡ ይታወሳል።(አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ብልጽግና ፓርቲ በትግራይ ክልል በሁሉም ወረዳዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቅርቡ እንደሚከፍት የፓርቲው የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙት ኃላፊ አወሉ አብዲ  ገለጹ።አውሎ እንደገለጹት ብልጽግና አገር አቀፍ ፓርቲ በመሆኑ ከትግራይ ክልል ጋር በሚኖረው ሕገ መንግሥታዊ ግንኙነት መሠረት አደረጃጀቱን በማስፋት በቅርቡ በክልሉ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ጽሕፈት ቤቶችን ይከፍታል ብለዋል፡፡(አዲስ ዘመን)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

 

መነሻውን ከሚሴ በማድረግ ወደ ደራ በሕገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር 400 ጩቤዎችን ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ። የአስተዳደሩ ፖሊስ ጽ/ቤት ሓላፊ ዋና ኢንስፔክተር መርሐጽድቅ ታዬ፣ በዛሬው ዕለት የካቲት20/2012  ከጠዋቱ 12 ሰዓት አካባቢ 400 ጩቤ፣ 4 የክላሽ ካርታ መያዣ እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጉንዶ መስቀል ቅርንጫፍ አካውንት ደብተር 82 ሺህ 444 ብር ይዞ ሲዘዋወር የነበረን ተጠርጣሪ የወረዳው ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተናግረዋል።(ኢቢሲ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በፈረንጆች 2019 ኢትዮጵያን ከጎበኙ 41 ሺህ 837 ቻይናውያን ጎብኝዎች 157 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መገኘቱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘገበ። ቻይና ከአሜሪካና እንግሊዝ ቀጥላ ኢትዮጵያን ከሚጎበኙ ሀገራት መካከል አንዷ ስትሆን በ2019 በተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ቻይናውያን 157 የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን በሚኒስቴር መስረያ ቤቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት እንደገና ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡የጎብኝዎች ቁጥር ከፍ በማድርግ የአገር ኢኮኖሚን ለማሻሻል በአሁኑ ሰዓትም ቻይናውያን ጎብኝዎች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ የሚያደርጉ በርካታ ስራዎች እተሰሩ ነው ብለዋል። (ሲ ጂ ቲ ኤን )

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እና ኢትዮሊዝ ከተሰኘ ድርጅት ጋር ግብርናን ሜካናይዝድ(ዘመናዊ) ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።ስምምነቱን በግብርና ሚኒስቴር የእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሳኒ ረዲ፣ የኢትዮሊዝ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ጪምዶ አንጫላ ተፈራርመውታል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here