የአሜሪካ የአለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ ዩኤስ ኤድ ኢትዮጵያ ለምታካሂዳቸው ምርጫዎች የሚውል ከ 30 ነጥብ አራት ሚሊዮን ዶላር ባለይ ድጋፍ አደረገ፡፡
የድጋፍ ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና የዩኤስ ኤድ ዳይሬክተር ሲን ጆንስ ዛሬ የካቲት 20/2012 ረፋድ ላይ በአዲስ አበባ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርመዋል።
ድጋፉ ቀጣዩ ምርጫ ተዓማኒ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ግልፅነት የሰፈነበት እንዲሆን የሚያደርጉ ስራዎች ለማከናወን ይውላል ተብሏል፡፡



