የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰራተኞች በዛሬው እለት መጋቢት 07/2012 ከቤት እንዲሰሩ ወሰነ።
ለቦርዱ ቴክኒካዊ ድጋፍ ከሚሰጡ የውጭ አገር ባለሙያዎች መካከል አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተጠረጠሩ ሲሆን ምርመራ ተደርጎ ውጤቱ እስኪረጋገጥ ድረስ ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል የተወሰደ እርምጃ እንደሆነ ቦርዱ አስታውቋል።
ግለሰቡ ከአንድ ወር በፊት ወደ አገር ውስጥ የገባ ሲሆን ቦርዱም ምልክቶቹ ከታዩበት ጊዜ አንስቶ ምርመራ እንዲደረግለት ጠይቆ ምርመራው እንዲካሄድ እየጠበቀ እንድሚገኝም ቦርዱ ይፋ አድጓል።



