ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ወሰኑ

0
532

ከዛሬ መጋቢት 07/2012 ጀምሮ ትምህርት ቤቶች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና ትላልቅ ስብሰባዎች ለ15 ቀናት እንደሚዘጉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘገበ።

የመጀመሪያ እና ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላ አገሪቱ ለኹለት ሳምንታት እንዲዘጉ የወሰኑ ሲሆን  የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደግሞ  ባሉበት ቦታ ሆነው ሳይወጡ እና ሳይገቡ ክትትል እየተደረገላቸው እንዲቆዩ መወሰናቸው ተገለጸ።

በእምነት ተቋማት የሚደረጉ ሰፋ ያሉ የአምልኮ ሥርዓቶች ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት እንዲቀንሱ የሚደረግበትን አግባብ የሃይማኖት መሪዎች እንዲያመቻቹም ጠይቀዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here