ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክ ፌዴሬሽን በኮሮና ቫይረስ ምክኒያት የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል

0
1263

‹‹እኔ አሻንጉሊት አይደለሁም›› አትሌት ደራርቱ

 

በመጪው ሃምሌ ወር ይካሄዳል ተብሎ ለሚጠበቀው የቶኪዮው ኦሎምፒክ አትሌቶች ሆቴል ገብተው ይሰልጥሉ አይሰልጥኑ የሚለው የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቃላት ጦርነት ውስጥ ግብተዋል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ደራርቱ ቱሉ ከ 100 በላይ አትሌት አንድ ሆቴል በግባት የለበትም፣ ይህ ለህይወታቸው ያሰጋል በሚል ውሳኔ ማሳለፋቸው ይታወሳል።

ይህንን የተቃወመው በአሸብር ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው የኦሎምፒክ ኮሚቴ ግን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባገኘሁት ፈቃድ መሰረት አትሌቶችን ሆቴል አስገባለሁ ሲል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይ አትሌት ሃይሌ ገብረ ስላሴ እና ገብረ እግዚአብሄር ገብረ ማሪያም እንዲሁም አባ ዱላ ገመዳ ተገኝተው ነበር።

‹‹ሃይሌን እና ገብረ እግዚአብሄር ራሳቸው ቢሆኑ የማያደርጉትን ለሌላ አትሌት ለምን ይወስናሉ፤ ከኮሚቴው ይልቅ እኛ እንቀርባቸዋለን›› ሲሉ አትሌት ደራርቱ ወቅሰዋቸዋል። ‹‹የአትሌቶች ዝግጀት አካላዊ ንክኪ ያለው በመሆኑ፤ ምግብ ሲበሉ እና በአውቶቡስ ሲጓጓዙ የኮሮና ቫይረስ መጋለጣቸው ስለማይቀር ይህንን ውሳኔ አሳልፌአለሁ›› ሲሉም ዛሬ ጠዋት በኢቲቪ ቀርበው ተናግረዋል።

‹‹እኔ አሻንጉሊት አይደለሁም፣ ልንሰራ ነው የተቀመጥነው›› ያሉት ደራርቱ ‹‹የፈረደበት ብሄር ገበቶ ከሆነ ቢታረም፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ሎጂሰትቲክስ እንጂ እንደዚህ አይነት ውሳኔ መስጠት አይችልም። አትሌቶቹ ልጆቼ ናቸው፤ ባሉበት ልምምድ መስራታቸውን ይቀጥላሉ፤ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እያለ ያለው ግብፅ አባይ ላይ እያለች ያለውን ነው፤ እንዴት ነው በአትሌቲክስ ጉዳይ ፌዴሬሽኑ የማያገባው›› ሲሉ ደራርቱ ተናረግዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here