ትምህርት ቢዘጋም ተማሪዎች ተሰብስበው መዋላቸውን አላቆሙም

0
622

ከ መዋለ ህፃናት እስከ መሰናዶ ያሉ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በሚል ለ15 ቀናት እንዲዘጉ መንግስት ቢወስንም ተማሪዎቹ ግን በሰፈር ውስጥ ተሰብስበው በጨዋታ እሳለፉ ነው።

በምትኖርበት ፒያሳ አካባቢ ተማሪዎች ልክ እንደ ክረምት ወራት ሰፈር ውስጥ ተሰብስበው በመጫወት ወይም ዘመድ በመጠየቅ እያሳለፉ እንደሆነ የሶስት ልጀች እናት የሆነችው ማህሌት መላኩ ትናገራለች፡፡ ምንም እንኳን እርሷ ልጆቿ ከሌሎች ልጆችም ሆነ አዋቂዎች ተለይተው እዲቆዩ ብታደርግም የአካባቢው ነዋሪ ይህንን ባለማድረጉ ምክኒያት በጎረቤቶቿ ወቀሳ ልጆቿ ወጥተው እንዲጫወቱ መፍቀድ ጀምራለች፡፡

በሌላ በኩል በመርካቶ ነጋዴ የሆነው ዳንኤል መኩሪያ የሥራ ባህሪው ብዙ ሰዎችን እንዲያገኝ ስለሚያስገድደው ራሱን በተቻለ መጠን በእድሜ ከገፉ ከቤተሰብ አባለቱ አርቋል፡፡

‹‹የ12 ዓመት ሴት ልጄ እና የ10 ዓመት ወንድ ልጄ ከቤት እንዳይወጡ መፅሃፎችን በመግዛት እና ፊልሞችን እዲያዩ አደረጋለሁ፡፡ ከቤት ውጪም እናታቸው የቤት እመቤት በመሆኗ ከሌሎች ሰዎች ሳይቀላቀሉ እንዲዝናኑ አድርጋ ራሷ ትመልሰቸዋልች›› ሲል ለአዲስ ማዳ አስረደረቷል፡፡

ተማሪዎች ዕረፍት መሆናቸውን ተከትሎ ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ የሚያስረዱት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የነርሲንግ ክፍል ዳይሬክተር ደረጄ ባይሳ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በአጠቃላይ ይህ ቫይረስ ሕጻናትና ታደጊዎች ላይ የሞት አደጋ አያድርስ እንጂ ህፃናት ለቫይረሱ ተጋላጭ አይደሉም የሚል ድምዳሜ የለም፤ እንደ ባለሞያው ከሆነ፡፡  ስለዚህም ቤተሰብ፣ማሕበረሰብ እና መንግስት ከትምህርት ያረፉትን ህፃናት እና ታዳጊዎች እንቅስቃሴ እንዲቀንሱ በማድረግ እና ማህበራዊ ፈቀቅታም ለእነርሱም ጭምር የሚሰራ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረተርያት ጽኅፈትም ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው የትምህርት ሬዲዮ ጣቢያን መከታተል ይችላሉ ሲል መልዕክቱን በፌስቡክ ገጹ ላይ ይፋ አድርጓል።

የሃኪሙ ምክሮች ባጭሩ

  • ትምህርት ቢዘጋም የትምህርት ዘመኑ ስለሚቀጥል ጥናታቸውን መቀጠል
  • ከቤት አለመውጣት
  • ከማሕበረሰቡ ጋር ያላቸውን ቅርርብ መቀነስ
  • መጨባበጥ ማቆም
  • አዋቂዎችም ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ቤታቸው ሲገቡ እጃቸውን በሳሙና መታጠብ እና ልጆቻውንም ይሁን ቤተሰቡውን አለመጨበጥ
  • ቫይረሱ ሕጻናትን አያጠቃም የሚለውን በሳይንስ ያልተረጋገጠ ሃሳብን ማስወገድ
  • ቤት ውስጥም ቢሆን ተቀራርቦ አለመቀመጥ
  • ቤት ውስጥ መስኮት እና በሮችን መከፈት

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here