በአዲስ አበባ ከተማ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በውጪ አገራት ዜጎች ላይ ትንኮሳ እየተፈፀመ ነው

0
580

በአዲስ አባባ ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች የውጪ አገር ዜጎች ላይ የኮሮና ቫይረስን መሰረት በማድረግ የሚፈፀሙ ትንኮሳዎች አግባብነት የሌላቸው ሕግ ወጥ ድርጊት መሆናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ቦሌ ሚካኤልና መስቀል ፍላወር በተባሉ አካባቢዎች ላይ የውጭ አገር ዜጎች እና የአየር መንገድ ሰርቪስ አሽከርካሪዎች እና ሰራተኞች ላይ ያነጣጠረ ትንኮሳና ዛቻ እየደደረሰባቸው እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ጥቆማ እንደደረሰው ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ከቫይረሱ ወረርሽን ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ ምክንያት የሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት ትንኮሳና ዛቻ ተገቢነት የሌለው ሕገ ወጥ ተግባር ከመሆኑም ባሻገር የአገራችንን የውጭ ግንኙነት የሚያበላሽ ኢ ሰብአዊ ድርጊት በመሆኑ ሕብረተሰቡ ከእነደዚህ ዓይነት ተግባራት ሊቆጠብ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

በውጭ አገር ዜጎች ላይ የሚደረገውን ትንኮሳ ለመከላከል ፖሊስ የሚያደርገውን የወንጀል መከላከል ተግባር በመደገፍ የከተማችን ነዋሪዎች ተገቢውን መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን እያቀረበ ሲሆን በሕገ ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 72 መጋቢት 12 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here