ዳሰሳ ዘ ማላዳ (መጋቢት 17/2012)

0
1423

 

በኮንቴይነር ውስጥ ሞተው የተገኙት ኢትዮጵያዊያን ቀብር በሞዛምቢክ ተፈጸመ

 

ከማላዊ ወደ ሞዛምቢክ ሲጓዝ በነበረበት የጭነት መኪና ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኙት 64 ኢትዮጵያዊያን ቀብር ተፈጸመ።

የሞዛምቢክ ባለስልጣናት እንዳሉት በኮንቴነር ውስጥ ሞተው የተገኙትን ኢትዮጵያዊያን የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ማገቢት17/201 እዚያው ሞዛምቢክ ውስጥ ተፈጽሟል ብለዋል። ማክሰኞ ዕለት አስክሬናቸው የተገኘው ኢትዮጵያዊያን በአየር እጥረት ታፍነው ሳይሞቱ እንደማይቀር በስፋት ተገምቷል። (ቢቢሲ አማርኛ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በክልሉ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሰለፈ ሲሆን

በዚህም የክልሉ መንግስት ካቢኔ ስራ አስፈፃሚ በትናንትናው እለት መጋቢት 16/2012 ምሽት የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ውሳኔዎችን ማሳለፉን ገልፀዋል።

ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በሰጡት መግለጫም ዝርዝር ውሳኔውን ይፋ ያደረጉ ሲሆን፥ በትግራይ ክልል ከገጠር ወደ ከተማ፤ ከከተማ ወደ ገጠር እንዲሁም ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረጉ ዝውውሮች ተከልክለዋል። ህዝብ በብዛት የሚሰበሰብባቸው የገበያ ማዕከላት፤ ማህበራዊ ግንኙነቶች የሚከናወንባቸው እንደ ሰርግ፣ ተስካር እና መሰል ክንውኖች እንዲሁም በክልሉ የሚደረጉ የእግር ኳስ ጨዋታዎች፣ የንግድ ተቋማት፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ጫት ቤቶች፣ የምሽት መዝናኛ ክለቦች እና ሌሎችን ህዝብ በብዛት የሚሰበሰብባቸው ተቋማት እንዲዘጉ ተወስኗል። በክልሉ የሚካሄዱ ማናቸውም ስብሰባዎች መታገዳቸውንም ገልፀዋል የመንግስት ሰራተኞችን በተመለከተም ነብሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች፣ እድሜያቸው ለጡረታ የተቃረቡ እና ለረጅም ጊዜ የቆየ የጤና እክል ያለባቸው ሰዎች በቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑንም አስታውቅዋል።(ፋና ብሮድካስቲን ኮርፖሬት)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ከአየር መንገድ ጠፍተው ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅዋል የተባሉ ግለሰቦች የገቡት የግዴታ ለይቶ ማቆየት ከመተግበሩ በፊት ነው  ሲል  የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።መጋቢት 15/2012 ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ የመጡ አንድ መንገደኛ ወደ ሀገር ከገቡ በኋላ ከአየር መንገድ በመጥፋት ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለዋል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ላይ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማጣራት ማካሔዱን ጤና ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን ግለሰቧ ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ መጋቢት 08/2012ከባለቤታቸው መምጣታቸውንና ወደ አገር ሲገቡ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ የሚደረገውን የልየታ ሂደት ውስጥ ማለፋቸውን ገልጿል። ግለሰቦቹ የገቡት የግዴታ ለይቶ ማቆየት ከመተግበሩ በፊት መሆኑንም አመልክቷል።(ኢቲቪ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በቅርቡ በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተሾሙት አምባሳደሮች ምደብ ቦታ በዛሬው እለት መጋቢት17/2012 ይፋ ተደረገ። ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት የካቲት 24/2012 ይፋ መደረጉ የሚታወስ ሲሆን፥ በዚሁ መሰረት አምባሳደሮቹ የሚመደቡባቸው አገራት ከዚህ በሚከተለው መሰረት ተወስኗል።

ባለሙሉ ስለጣን አምባሳደሮች፦

 1. አምባሳደር ብርሁኑ ፀጋዬ አውስትራሊያ ካንቤራ
 2. አምባሳደር ያለም ፀጋይ ኩባ ሃቫና
 3. አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ቤልጄም ብራሰልስ
 4. አምባሳደር ዶክተር ማርቆስ ተክሌ ግብጽ ካይሮ
 5. አምባሳደር ባጫ ጊና ሞሮኮ ራባት
 6. አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ ሱዳን ካርቱም
 7. አምባሳደር ምህረታብ ሙሉጌታ ኤርትራ አስመራ
 8. አምባሳደር ነብያት ጌታቸው አልጀሪያ አልጀርስ እንዲሁም
 9. አምባሳደር ተፈሪ መለስ እንግሊዝ ለንደን እንዲሰሩ ተመድበዋል።

እንዲሁም አምባሳደሮች

 1. አምባሳደር አድጎ አምሳያ ስዊድን ስቶክሆልም ምክትል ሚሲዮን መሪ
 2. አምባሳደር ጀማል በከር ባህሬን ማናማ ቆንስል ጄኔራል
 3. አምባሳደር አብዱ ያሲን ሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ቆንስል ጄኔራል
 4. አምባሳደር ለገሠ ገረመው ካናዳ ኦታዋ ቆንስል ጄኔራል
 5. አምባሳደር እየሩሳሌም አምደማርያም የተባበሩት አረብ ኢሚሪቶች ዱባይ ቆንስል ጄኔራል
 6. አምባሳደር ሽብሩ ማሞ አሜሪካ ሚኒሶታ ቆንስል ጄኔራል እንዲሰሩ ተመድበዋል።

አምባሳደሮቹ በተመደቡባቸው ሀገራት የፕሮቶኮል አሰራር መሰረት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቆ በቅርቡ
ወደ ምድብ ቦታቸው ተንቀሳቅሰው ስራቸውን በይፋ የሚጀምሩ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።(የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በይቅርታ እንዲፈቱ ከተወሰነላቸው መካከል 561 ታራሚዎች ዛሬ መጋቢት17/2012 ተፈቱ። ትናንት የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሲባል 4 ሺህ 11 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ተከትሎ የህግ ታራሚዎች እየተፈቱ ይገኛሉ። ዛሬ ከተፈቱት ውስጥ 20 ነፍሰ ጡሮችና ከህጻናት ጋር የታሰሩ እናቶች የሚገኙበት ሲሆን በአጠቃላይ ከተፈቱት መካከል 161 ሴቶች ናቸው ተብሏል። (ኢዜአ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ላይ ጥናት ለማካሄድ 10 ሚሊየን ብር መደበ። በዛሬው እለት መጋቢት17/2012 በኮቪድ19 ላይ ጥናት የሚያኪያሂድ የጥናት ቡድን የተቋቋመ ሲሆን ቡድኑ ጥናቱን ለመጀመር ይችል ዘንድ ከተመደበው አጠቃላይ ፈንድ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ብር ወጪ ሆኖ የተሰጠው ሲሆን የጥናት ቡድኑ አባላት ከተለያዩ ኮሌጆችና ተቋማት ከልዩ ልዩ መስክ የተውጣጡ ምሁራንን ያካተተ ሲሆን የመጀመሪያ ስብሰባውንም በዛሬው እለት መጋቢት 17/2012  አድርጓል። ለጥናቱ የተመደበው ቀሪው ገንዘብ በውድድር ላይ ተመስርቶ በመሰል ጥናት ለመሳተፍ ለሚሹ የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ስታፍ አባላት የሚቀርብ እንደሚሆን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት  ጣሰው ወልደሐና(ፕ/ር) አስታውቀዋል።

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

በምዕራብ ኦሮሚያ ባልታወቊ ሰዎች የታገቱ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ «17 አማራ ተማሪዎች ጉዳይን መንግሥት ግልጽ እንዲያደርግ» ሲል ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ። በኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የኮሮና ተሐዋሲ ሥርጭትን በመስጋት በሚዘጉበት በአኹኑ ወቅት መንግሥት የታገቱ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ ስለወሰዳቸው ርምጃዎች ግልጽ እንዲያደርግ አምነስቲ የጠየቀ ሲሆን ቫይረሱ በኢትዮጵያ የፈጠረው «ስጋት እና ርግጠኛ ያልሆነ ነገር የሚወዷቸው ልጆቻቸው የት እንደሚገኙ አንዳችም መረጃ የሌላቸው ቤተሰቦችን ብርቱ ሐዘን አባብሶታል» ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታውቋል።(ዶቼቨለ)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here