ዳሰሳ ዘ ማለዳ (መጋቢት18/2012)

0
813

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በቀጥታ የሚፈጸምን የትኬት ሽያጭ አቆመ

 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጥታ የሚፈጸምን የትኬት ሽያጭ ማቆሙን ያስታወቀ ሲሆን ለየትኛውም ጉዞ የሚፈጸምን የትኬት ሽያጭ በኢንተርኔት አማካኝነት እንደሚሰጥ ገልጿል።

እርምጃው እየተስፋፋ የመጣውን የኮቪድ19 ስርጭትን ለመግታት በማለም የተወሰደ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በዚህም የትኬት መሸጫ ቢሮዎች ከፊታችን ሰኞ መጋቢት21/2012  ጀምሮ ለጊዜው ይዘጋሉ ብሏል።

ደንበኞችም አገልግሎቱን አየር መንገዱ ባዘጋጃቸው የሞባይል መተግበሪያዎችና በባንኮች ማግኘት እንደሚችሉም ተነግሯል። (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኮቪድ19 ለመከላከል የክልሉ መንግስት ያወጣውን መመሪያ በማይተገብር ኃላፊ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ አስጠነቀቁ። ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ መጋቢት18/2012  ከካቢኔ አባሎቻቸውጋር ባደረጉት ምክክር የተለዩ ሠራተኞች ከስራ ተገልለው እንዲቆዩ የሚለውን መመሪያ በተለያዩ ምክንያቶች እየተገበሩ አይደለም ብለዋል።(ዶቼቨለ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በኢትዮጵያ ለኮቪድ19 የሚሆን መድሃኒት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክነሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂነር) ለአዲስ ማለዳ አረጋገጡ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር ኢንጂ.)፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር  ሊያ ታደሰና  (ዶ/ር) ከኢትዮጵያዊያን የባህል ሃኪሞች ጋር እና የህክምና ተመራማሪዎች ጋር በመሆን የአገር በቀል እውቀቶችን በሳይንሳዊ ሂደቶች በማሳለፍ ለኮቪድ 19 ህክምና የተዘጋጀውን መድሃኒት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላቸውን ስራ በመስራት ላይ እንደሆነም ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።(አዲስ ማለዳ)
…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኮቪድ19  ስርጭትን ለመከላከል የወጡ መመሪያዎችን በማይተገብሩ ዜጎች ላይ ከዛሬ መጋቢት 18/2012 ጀምሮ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ፌደራል ፖሊስ ገለጸ።

የቫይረሱን ሥርጭት  ለመከላከል መንግስት ያወጣቸውን መመሪያዎች በአግባቡ በማይተገብሩ ዜጎች ላይ የፌደራል ፖሊስ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ ከዛሬ ጀምሮ መውሰድ ሊጀምር መሆኑን ፋና ብሮድካስቲግ ዘግቧል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጀኔራል ኮሚሽነር እንደሻው ጣሰው በጉዳዩ ላይ በሰጡት መግለጫ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት መንግስት ዜጎች መጨባበጥን እንዲያቆሙ፣ ርቀትን እንዲያስጠብቁና ስብሰባ እንዲያቆሙ መመሪያ ቢያወጣም በአግባቡ እየተተገበረ አይደለም ብለዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አንደገለጸው በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 16 ደርሷል።

ዛሬ መጋቢት 18/2012 በኮቪድ19 በሽታ የተያዙ ተጨማሪ አራት ሰዎች መገኘታቸውን ሚኒስቴሩ በመግለጫ ላይ አስታውቋል።በዚህም በቫይረሱ የተያዙ አራት ተጨማሪ ሰዎች በመገኘታቸው በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ስድስት ደርሷል።(ጤና ሚኒስቴር)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

አዲስ አበባ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ባላት እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ሊጣል እንደሚችል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ  ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ተናገሩ።

“በከተማችን መግቢያና መውጫዎች በተለይ የወጣቶች ያልተለመደ እንቅስቃሴ ከወትሮው በጨመረ መጠን እያስተዋልን ነው። ሲሉም በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስፍረዋል። ለጊዜው ጥያቄ ተገቢውን ሁሉ ለማድረግ በምናደርገው ጥረት ወደከተማችን እና በከተማች የሚደረግ እንቅስቃሴን በአንክሮ የምንከታተል መሆኑን ለሕዝባችን ጤና እና ደህንነት ጠንቅ ይሆናል ብለን በምንወስን ጊዜም ተገቢውን እርምጃ እንደምንወስድ በመግለፅ እንድትጠነቀቁ አሳስባለሁ” ብለዋል።

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በሃሰት የኮቪድ19 አለብኝ በማለት ወደ 8335 የደወለችው የጎንደር ከተማ ነዋሪ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለች። ወጣቷ በጎንደር ከተማ ቀበሌ 16 በግል ስራ ተቀጥራ የምትሰራ ሲሆን ከአረብ ሃገር በቅርቡ እንደመጣች በመግለጽ የበሽታው ምልክት እንደታየባትና እርዳታ እንደምትሻ ተናግራ ነበር ብሏል የከተማዋ ፖሊስ።
ይህንን ተከትሎ የክልልና የዞን የጤና ባለሙያዎች ተነጋግረው ልጅቷን ሲያፈላልጉ ስልኳን በመዝጋት ተደብቃ የነበር ቢሆንም ፣ በ ጂ ፒ ኤስ ተፈልጋ ተገኝታለች ተብሏል።(ዶቼቨለ)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here