በምሥራቅ ጎጃም ዞን በትራፊክ አደጋ የኹለት ተማሪዎች ሕይወት አለፈ

0
410

ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ይዞ ሲጓዝ የነበረ መኪና የትራፊክ አደጋ ደርሶበት የኹለት ተማሪዎች ሕይወት አለፈ።
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደየ ቤተሰቦቻቸው ይዞ በመሄድ ላይ የነበረ መኪና በመገልበጡ ኹለት ተማሪዎች ሲሞቱ በ22 ተማሪዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።

አደጋው የደረሰው በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ጢቅ የትኖራ ቀበሌ መጋቢት17/2012 ሌሊት ስምንት ሰዓት ላይ ነው። የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ከዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ይዞ ወደ አማራ ክልል በመግባት ላይ እያለ ነው የትራፊክ አደጋ ያጋጠመው ሲል ነው የአማራ ብዙኀን መገናኛ ድርጅት የገለጸው።
በአጠቃላይ አደጋው በኹለት ተማሪዎች ላይ ሞት፣ በ18 ተማሪዎች ቀላልና በአራት ተማሪዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በደጀን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና በደብረማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ እንደተደረገላቸው እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ተናግረዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 73 መጋቢት 19 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here