ኮሮናን ለመዋጋት ሩዋንዳ 109 ሚሊዮን ዶላር ብድር አገኝች

0
350

ሩዋንዳ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል 109.4 ሚሊዮን ዶላር ብድር ከዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ.አም.ኤፍ) በማግኝት የመጀመሪያዋ የአፍሪካ አገር ሆናለች። ብድሩን በንግድ፣ በቱሪዝም እና በውጪ ምንዛሬ ክምችት በኩል ያሉባትን ችግሮች ለመቅረፍ የምትጠቀመው ሲሆን አብዛኛውን ብድር ግን ለጤናው ዘርፍ እንደምታውለው ዲደብሊው አፍሪካ (ዶቼቬለ) ዘግቧል።
ሩዋንዳ 84 ዜጎቿ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተጠቁ ሲሆኑ ሙሉ በሙሉ በቤት ውስጥ መቆየትን ተግባራዊ በማድረግ መንግሥት ለዜጎቹ ምግብ እና አስፈላጊ የጤና መጠበቂያዎችን እያቀረበ ይገኛል።
ይህ የተገኘ ብድር ሩዋንዳ ቫይረሱን ለመከላከል በምታደርገው ጥረት ያግዛታል ተብሎ የታመነ ሲሆን፣ ድጋፎችም በተመሳሳይ ይጠበቃሉ። አፍሪካ የቫይረሱን ወረርሽኝ ለመከላከልና ባለበት ደረጃ ለመቆጣጠር ሰፊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት በተደጋጋሚ የተጠቀሰ ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅትም የአፍሪካ አገራት ምላሽ ለመስጠትና መቋቋም እንዲያስችላቸው በዝግጅት እንዲጠናከሩ ቅስቀሳ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

ቅጽ 2 ቁጥር 74 መጋቢት 26 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here